እ.ኤ.አ ሚያዝያ 11/ 2021 የሚኒያፖሊስ ፖሊስ ኦፊሰር ኪም ፖተር ዳኡንት ራይት የተባለውን የሀያ አመት ወጣት የትራፊክ መኪና ማቆምያ ጋር ተኩሳ ገላዋለች። የዚህን የ 20 አመት ጥቁር አሜሪካዊ ወጣት ህይወት በመቅጠፏ ባለፈው ሳምንት ለሁለት አመታት ብቻ በእስር እንድትቆይ ተፈርዶባታል። በሚያስገርም ሁኔታ የቀድሞ የሚኒያፖሊስ ጥቁር ሱማሌ-አሜሪካዊ የፖሊስ ኦፊሰር የሆነው ሙሐመድ ኑር በ ሀምሌ 15/2017 ላይ ጀስቲን ሩስዝይክን ተኩሶ በመግደሉ የ 12 አመት የእስር ቅጣት ተጥሎበታል። ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም ጸጉር የነበራት ጀስቲን ከዳኡንት ጋርም ይሁን በተለምዶ ከሚታወቁ የፖሊስ ተጎጆዎች የሚያመሳስላት ነገር የለም።
ኪም ፖተር ዳኡንትን በትራፊክ መብራት ዳር ባስቆመችበት ጊዜ ምልምል የ ፖሊስ አባላትን እያሰለጠነች ነበር። የዳኡንትን እጅ ልታስር በሞከረችበት ወቅት ወደኋላ በማፈግፈጉ ብቻ መሳርያዋን ልትመዝ ችላለች። እንደ ተከሳሽዋ ንግግር ከሆነ በግዜው ቴዜር የተባለ ጊዚያዊ አቅም ማዳከምያውን እንጂ መሳርያ ለመጠቀም አስባ አልነበረም። ይሁን እንጂ ቴዘርን እና ሽጉጥን በተቃራኒ በኩል ወገብ ጋር አድርጎ ማስቀመጥ የፖሊሶች ደንብ ነው። ይህን አዲሷ የኪም ሰልጣኝ የምታስታውሰው ቢሆንም የ 26 አመቷ ኪም ግን ዘንግታዋለች።
ኪም በስህተህ ሽጉጧን አውጥታ በተደጋጋሚ ‘ቴዘር’ ብላ በመጮህ የሽጉጧን ምላጭ ስባ ዱኣንትን ለሞት ዳርጋዋለች። የኪም በ ዳኡንት ላይ የነበራት ፍራቻ እና ሽጉጧን ይዛ በሽራፊ ሰከንዶች ውስጥ በሰራችው ስህተት እና የተከተለው ፀፀት ከ ቀድሞው የሚኒያፖሊስ ፖሊስ ኦፊሰር መሀመድ ኑር ጋር የሚመሳሰል ነው።
በ ሀምሌ 15/2017 ነበር ሙሐመድ የጀስቲንን የ 911 የአደጋ ጊዜ ጥሪ የመለሰው። ከቤቷ ጀርባ የሰማችው ድምጽ የፆታዊ ጥቃት ሊሆን ይችላል ብላ በመገመት ነበር ለማመልከት የደወለችው። ሙሐመድም ወደ ቦታው የሄደው ከስራ ባልደረባው ማቲው ሃሪቲ ጋር ነበር። ማቲው ለፍርድ ቤት በሰጠው ቃል ቦታው ላይ በነበረበት ጊዜ ጀስቲን መኪና ስታስነሳ በሰማው ድምጽ ፈርቶ እንደነበር ይናገራል። በዚህ ግዜ ነው ሙሐመድ ባልደረባው ማቲው “ወይኔ ፈጣሪ” ሲል የሰማው። በዚህ መሀከል ነው ጀስቲን እጅዋን ስታነሳ ሙሐመድ ኑር በቅፅበት ቃታውን ለመሳብ የተገደደው። በ ኪም ፖተር የተፈፀውም ቅፅበታዊ እርምጃ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር።
ልብሷ ላይ ያለው ካሜራ እንደሚያሳየው ኪም ዳኡንት ላይ ከተኮሰች በኋላ “ተኮስኩበት” ብላ በሲቃ ጮሃለች። በተመሳሳይ ሁኔታ መሀመድ “ወደ ወይዘሮ ጀስቲን ቀረብ ብሎ እያጣረች ባለችበት ሰአት ስደርስ ጥፋተኝነት ተሰማኝ። በዛች ቅፅበት ነው ልክ እንዳልነበርኩ ተረዳሁ።” ብሏል።
ዱኣንትን መግደል ልክ እንዳልነበረው ሁሉ ጀስቲንን መግደልም ልክ አልነበረም። የሁለቱ ፖሊስ ኦፊሰሮች ድሪጊት ልክ አለመሆኑን ከተስማማን እጅግ የተራራቀ ውሳኔ ለምን ተሰጣቸው? የካቲት 18/2022 ላይ የሚኒኣፖሊስ ፍ/ቤት ኪም ላይ የ ሁለት አመት የፈረደባት ቢሆንም እስራቱ ለ24 ወራት ይቆያል ማለት አይደለም። ለ 16 ወራት በእስር ከቆየች በኋላ ክትትል እየተደረገላት የምትለቀቅ ይሆናል።
የዳኡንት እናት ኬቲ ራይት ዳኛው በልጅዋ ገዳይ ላይ ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣልባት ዳኛውን ብትጠይቅም በተቃራኒው በተሰጠው ውሳኔ መደናገጧ ግን አልቀረም። ኬቲ ኪምን ይበልጥ ያስጨነቃት ተኩሳ የገደለችው ዱኣንት ሳይሆን ስራዋ እና የወደፊት እጣ ፈንታዋ ነው። ትላለች አስከትላም “የዱኣንትን ህልም ነጥቀሻል።” ስትል የፖሊስ ኦፊሰርዋን ኮንናለች። በዳኛው ውሳኔ የተከፉት የ ራይት እናት “ኪም ፖተር ልጄን በሚያዛ 11 ገላዋለች። ዛሬ ደግሞ የፍትህ ስርአቱ በውሳኔው በድጋሜ ገሎታል።” ብላለች።
በሌላ በኩል ዳኛው ረጊና ይሀንን ጉዳይ ከ ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር አነጻጽሮታል። “ይህቺ ፖሊስ በጉልበቷ የተጎጂው አንገት ላይ ጉልበቷን በማሳረፍ ለዘጠኝ እና ግማሽ ሰከንዶች ትንፋሽ እስኪያጥረው ድረስ ቆማበት ሳይሆን በስህተት የሰራቸው ወንጀል ነው።” ብሏል።
ዳኛው የኪምን ወንጀል ከጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ጋር ሲያነፃፅሩ የሙሐመድ ቤተሰቦች በተራቸው የኪምን ፍርድ እስር ቤት ውስጥ ካለው ሙሐመድ ጋር እያነጻጸሩት ይሆናል። ሁለቱም ተከሳሾች ግድያውን የፈጸሙት በስህተት ከሆነ የተወሰነባቸው ውሳኔ ግን ይህንን አያሳይም። መሀመድ ለሰራው ስህተት የ 12 አመት እስራት ተፈርዶበታል።
ሙሐመድ ስራ ላይ ሆኖ ተኩሶ በመግደል የመጀመርያው የሚኒሶታ ፖሊስ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ ከ አንድ አመት በፊት በ 2016 ኦፊሰር ጄሮኒሞ ያኔዝ ፊላንዶ ካስቲልን ተኩሶ ገድሎታል። ፊላንዶ ከሴት ጓደኛው ጋር መኪና ሲነዳ ነበር ኦፊሰሩ ያስቆመው። ኦፊሰር ጄሮኒሞ ካስቲል ሽጉጡን እንዳያነሳ ይነግረዋል። ፊላንዶም “አላወጣሁም” ሲል መለሰ። ጄሮኒሞ ደጋግሞ “ ሽጉጥ እንዳታወጣ” ሲል የፊላንዶ ፍቅረኛ “እያወጣ አይደለም” እያለች የነበረ ቢሆንም ጄሮኒሞ ፊላንዶ ላይ ለሰባት ጊዜ ያህል ተኩሶበትላ። ፊላንዶ ከ20 ደቂቃ በኋላ በሄኔፒን የህክምና ማእከል ሞተ። ጄሮኒሞም በአምስት ቀናት ውስጥ ከሁሉም ክሶች ነጻ ተባለ።
እንደ እድል ሆኖ የመሀመድ ጠበቆች ለመሀመድ መሟገታቸውን አላቆሙም። አቃቤ ህግ ፒተር ዎልድ “ኑር በሽራፊ ሴኮንዶች ውስጥ እርምጃ በመውሰድ ወይዘሮ ጀስቲንን በጥይት ተኩሶ የገደላት በነበረበት ፍርሃቻ ምክያት እንደሆነ ጥያቄ የለውም።” ብሏል። ሌላው ተከላካይ ጠበቃ ቶማስ ፕሉንኬት እንደተናገረው “ፍርድ ቤቱ መሐመድን ለ150 ወራት እስር ቤት እንዲቆይ በመወሰኑ ቅር ተሰኝተናል። መደረግ ያለባቸው ሂደቶች ላይ ምልከታ እናደርጋለን። ለመሀመድ ኑር መቆማችንን እንቀጥላለን።” ብሏል።
በመሀመድ ጠበቆች ያላሰለሰ ጥረት እና መሀመድን ለመደገፍ ለፍርድ ቤት በተላኩ በርካታ ደብዳቤዎች ምክንያት ጥቅምት 2021 የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀመድን የ3ተኛ ደረጃ ግድያ ጥፋተኛነት ሽሮታል። ከዚያም ከአምስት ዓመት በታች በእስር እንዲቆይ ተፈርዶበታል። ምን አልባትም የእስር ጊዜውን የሚጨርስ ከሆነ በዚህ ክረምት ሊፈታ ይችላል። በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመሀመድን የቅጣት ውሳኔ ቢቀንስም ቀድሞ ተፈርዶበት የነበረው የ12 ዓመት ተኩል ቅጣት በፍትህ አሰጣጡ ላይ ጥያቄን ያስነሳል ምክንያቱም የኪም የሁለት አመት የእስር ቅጣት ውሳኔ በኩልነትን ላይ የተመሰረተ ፍትህን ከመስጠት ጋር ሊጣረስ ይችላል።
ይህ የፍትህ አሰጣጥ ልዩነት የመጣው በፖሊሶቹ የቀለም ልዩነት ሳይሆን የተፈረደባቸው በተፈፀሙት ወንጀል ብቻ ነው ብሎ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ምን አልባትም የቀለም ልዩነት በራሱ ብዙውን ጊዜ ፍርድ እንዴት እንደሚሰጥ ይወስናል። እንዲሁም ተጎጂዎቹ በነሱ ላይ በተፈፀመው ወንጀል ብቻ እንጂ በ ቀለማቸው ልዩነት አይደለም የተፈረደላቸው ብሎ ለማለትም አስቸጋሪ ያደርገዋል።
እንደ እድል ሆኖ የመሀመድ ጠበቆች ለመሀመድ መሟገታቸውን አላቆሙም። አቃቤ ህግ ፒተር ዎልድ “ኑር በሽራፊ ሴኮንዶች ውስጥ እርምጃ በመውሰድ ወይዘሮ ጀስቲንን በጥይት ተኩሶ የገደላት በነበረበት ፍርቻ ምክያት እንደሆነ ጥያቄ የለውም።” ብሏል። ሌላው ተከላካይ ጠበቃ ቶማስ ፕሉንኬት እንደተናገረው “ፍርድ ቤቱ መሐመድን ለ150 ወራት እስር ቤት እንዲቆይ በመወሰኑ ቅር ተሰኝተናል። መደረግ ያለባቸው ሂደቶች ላይ ምልከታ እናደርጋለን። ለመሀመድ ኑር መቆማችንን እንቀጥላለን።” ብሏል።
በሙሀመድ ጠበቆች ያላሰለሰ ጥረት እና መሀመድን ለመደገፍ ለፍርድ ቤት በተላኩ በርካታ ደብዳቤዎች ምክንያት ጥቅምት 2021 የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀመድን የ3ተኛ ደረጃ ግድያ ጥፋተኛነት ሽሮታል። ከዚያም ከአምስት ዓመት በታች በእስር እንዲቆይ ተፈርዶበታል። ምን አልባትም የእስር ጊዜውን የሚጨርስ ከሆነ በዚህ ክረምት ሊፈታ ይችላል። በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመሀመድን የቅጣት ውሳኔ ቢቀንስም በተመሳሳይ ክስ ኪም የሁለት አመት እስር ተፈርዶባት በተቃራኒው እርሱ ላይ የ 12 አመት ተኩል ውሳኔ መስጠቱ የፍርድ ቤቱን ፍትሀዊነት ጥያቄ ውስጥ ይከታል።
ይህ የፍትህ አሰጣጥ ልዩነት የመጣው በፖሊሶቹ የቀለም ልዩነት ሳይሆን የተፈረደባቸው በፈፀሙት ወንጀል ብቻ ነው ብሎ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። በተደጋጋሚ እንደታየው የቀለም ልዩነት የፍርድ አሰጣጡን ይወስናል። ይህም ተጎጂዎቹ በፈፀሙት ወንጀል ብቻ ነው ፍርድ የተሰጣቸው ለማለት አዳጋች ያደርገዋል።