ኮንግረስማን ጆ ንጉሴ ከ 2019 ጀምሮ የኮሎራዶ አውራጃ ኮንግረስ አባል ሆኖ ማገልገል ከጀመረበት ግዜ አንስቶ ስኬታማ ሆኗል። ጆ በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ የመጀመሪያው ኤርትራዊ አሜሪካዊ ሲሆን በአውራጃው ስራ መስራት ከጀመረበት ግዜ ጀምሮ ስሙ በመግነኑ የኮንግረሱን ሀሳብ መያዝ ችሏል። በቅርቡ በቀጣይ አምስት አመታት ለኮሎራዶ የህዝብ እንቅስቃሴ ማሳለጫ የሚሆን 917 ሚሊየን ዶላር መሰብሰብ ችሏል። ከዚህም ውስጥ 54 ሚሊየኑን በያዝነው የፌብሯሪ ወር መቀበል ችሏል።
በአሜሪካ የሲቪል መሐንዲሶች ማህበር የ መሠረተ ልማት ደረጃ አስጣጥ መሰረት የኮሮላዶ ከተማ ባለበት የመሰረተ ልማት ጉድለት መሰረት የ C- ደረጃን አግኝቷል። ጆ ይህንን ደረጃ ለማሻሻል እና ችግሩን ለመፍታት ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር እየሰራ ይገኛል።
ጆ ” የሁለትዮሽ መሠረተ ልማት ሕግን የደገፍኩት ከተለያዩ የሃገራቱ መሪዎች ጋር በመነጋገር እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ ለአስርት አመታት ያህል የፈደራል መንግስቱ መሰረተ ልማትን ሳይሰራ በቆየባቸው ቦታዎች ካሉ ከንቲባዎች እና ካውንቲ ኮሚሽነሮች አመራር ጋር በመነጋገር ነው። በውይይቱ መጨረሻ ላይም ኮሮላዶ ለመሰረተ ልማቱ በአጠቃላይ 917 ሚሊዮን ዶላር እንዲያገኝ የመጀመርያው ሆና ተመርጧል።” ብሏል።
በአሜሪካ የብሔራዊ ኤክስፕረስ ትራንዚት የህዝብ ትራንዚት አስፈላጊ የሆነባቸውን በርካታ ምክንያቶችን ዘርዝሯል። ከምክንያቶቹ መካከል ጆ ያነሳው የአየር ብክለትን እና የትራፊክ መጨናነቅ መቀነስ ይገኙበታል።
ለትራንስፖርት ዘርፍ ድጎማ የተሰበሰበው ገንዘብ አዳዲስ የህዝብ መጓጓዣ ባሶችን፣ የባቡር ፉርጎውችን እና የመኪና ጥጋና ቦታዎችን ለመገንባት ይውላል። የተበላሹ ባቡሮችን፣ የህዝብ መጓጓዣ ባስ፣ እቃ መጫኛዎችን እና የ መጓጓዣ ቦታዎች መሰረተ ልማትን በመጠገን ስራዎችን የሚያሳልጥ ይሆናል። ለ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ የማህብረሰብ ክፍሎች መሰረተ ልማቶቹን ምቹ በማድረግ ተደራሽነቱን ከፍ ያደርገዋል።
ጆ ንጉሴ የግዛቱን የትራንስፖርት ጉዳዮች በማሻሻል ግንባር ቀደም በመሆኑ በዋሽንግተን ውስጥ ካሉ ቁልፍ አካላት ትኩረት አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ2019 እንደ አዲስ ተባባሪ ተወካይ ሆኖ በምክር ቤት አመራር ውስጥ እንዲያገለግል ተመርጧል። በ 2020 የዲሞክራሲያዊ ፖሊሲ እና ኮሚኒኬሽን ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ እንዲያገለግል ተመረጠ። በተጨማሪም በ 2021 ናንሲ ፔሎሲ ለትራምፕ ሁለተኛ የክስ ችሎት የፍርድ ቤት ክስ ማናጀር አድርጎ ሾመው። ጆ በትራምትፕ ክስ ላይ ስለ አሜሪካ እሴቶች እና የሁለትዮሽነት አስፈላጊነት ጥልቅ የሆነ ንግግር አቅርቧል።
ጆ ንጉሴ በአራተኛ አመት የስልጣን ዘመኑ መልካም ስምን አፍርቷል። ገና በ 37 ዓመቱ ስኬታማ መሆን የቻለው ጆ አሁንም የፖለቲካ ህይወቱን ለማሳደግ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።