መጋቢት 2020 አሜሪካውያን በ ጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ግድያ ሳይቀጣ እና እልባት ሳይገኝለት እንዳይቀር በትትብብር የቆሙበት ወሳኝ ታሪካዊ ግዜ ነበር። የአንድነቱ ፍሬም በሚኒሶታ ግዛት ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነበር። ግዜው ለመጀመርያ ግዜ ነጭ የ ፖሊስ ባልደረባ በስራ ላይ እያለ ተኩሶ ግድያ በመፈፀሙ ለመጀመርያ ጊዜ ለጥፋቱ እርምጃ የተወሰደበት ነበር።
ፍሬያማ ተስፋን ያዘለ የሚመስለው የፍትህ ስርዐቱ ምን አልባትም ያ አሳዛኝ ክስተት በድጋሚ ሊፈጠር እንደማይችል በህዝቡ ልብ ውስጥ አመኔታን ፈጥሮ ሊሆን ይችላል። በተለይም ሚኒያፖሊስ ውስጥ በሚገኘው የጆርጅ ፍሎይድ ምስል በታሪክነት ተስሎ በተቀመጠበት 38ኛው መንገድ ዳር እና ቺካጎ ኤቭ እንዲሁም በሁሉም ሚኒሶታ አከባቢዎች በድጋሚ በጭራሽ ሊከሰት ይችላል ተብሎ አይታሰብም። ይሁን እንጂ የዚህ አይነት አሳዛኝ ግድያዎች ዳግም መፈጠራቸው አልቀረም።
ከሀያ ሶስት ወራት በኋላ የካቲት 2 ላይ አሚር ሎክ ከንጋት በፊት የሚኒያፖሊስ ፖሊሶች ሳያንኳኩ ቤቱን ከወረሩት በኋላ ግድያ ተፈጽሞበታል። የ ፖሊስ ቡድኑ የአሚርን መኖርያ ቤት የከበቡት በግድያ ወንጀል ተጠርጣሪ የነበረውን የአሚርን የአጎት ልጅ ለመያዝ ነበር። ታድያ ይህ ክስተት በኢልሃን ኦማር የቀረበውን አዲስ ህግ ለማምጣት መንገድ ከፍቷል።
ኢልሃን “ፖሊሶች ለባለቤቱ ሳያሳውቁ የግለሰቡን ቤት በመውረር መግባት እስካሁን በሰው እና በንብረት ላይ ከባድ እና አስከፊ ጉዳቶችን አስከትሏል። ሳያንኳኩ ወደ ግለሰብ ቤት መግባት ካለ ምንም ገደብ፣ ህግ እና ደንብ እንዲሁም በሰዎችህ ህይወት ላይ ስለሚያመጣው ተጽዕኖ ቦታ ሳይሰጠው ስራ ላይ መዋሉ ምክንያታዊ አይደለም።” ብላለች።
በስተመጨረሻም ፖሊሶቹ የካቲት 8 ላይ የአሚርን የአጎት ልጅ አግኝተው አስረውታል። ይሁን እንጂ አሚር ጥፋተኛው በተያዘበት ጠዋት በመኖርያ ቤቱ ውስጥ ተገሎ ተገኝቷል። አሚር ላይ ጥይቱን የሳበው ፖሊስ ደሞዙ ሳይቋረጥበት ለተወሰኑ ጊዜያት ከስራ ውጪ ሆኗል።
የሚኒያፖሊስ ፖሊስ ጊዜያዊ አመራር የሆነችው ኤሚሊያ ሁፍማን “ፖሊሱ ወደ አሚር መኖርያ ቤት ከመግባቱ በፊት ጮክ ብሎ ‘የፖሊስ የፍተሻ ትዕዛዝ ነን!’ ሲል አሳውቋል።” ብላለች። ነገር ግን በፖሊሱ ልብስ ላይ ያለው ካሜራ ይህንን የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል። ይልቁንም ካሜራው የሚያሳየው ፖሊሶቹ ወደ መኖርያ ቤቱ እየተቻኮሉ በመሄድ ለራሳቸው እያሳወቁ እንደነበር ነው። ይህም ምን አልባት አሚርን አስደንግጦት ህጋዊ የሆነውን ሽጉጡን እንዲይዝ አድርጎት ይሆናል።
በተጨማሪም ኤሜሊያ የአሚር ሽጉጥ ፖሊሶቹ ላይ ያነጣጠረ ነበር ብላለች። ነገር ግኝ በድጋሚ ካሜራው እንደሚያሳየው ከሆነ የሽጉጡ ኢላማ መሬት ላይ ነበር። አሚር በተገደለበት ማግስት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሜሊያ አሚር ቀደም ብሎ በሌላ የግድያ ወንጀል ተጠርጣሪ የነበረ መሆኑን ገልፃለች። ይሁን እንጂ የፖሊስ ዘገባው በግልፅ እንደሚያሳየው ፖሊሶቹ የአሚርን ማንነት የለዩት ግድያው ከተፈጸመ ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነበር።
ለዚህ አሰቃቂ ግድያ ምላሽ በመስጠት በመጋቢት መጀመርያ ላይ ኢልሃን ኦማር እነዚህን የመሳሰሉ ግድያዎች እንዳይፈጠሩ ሊከላከል እንደሚችል የሚታሰብ ‘የአሚር ሎኬ ሳያሳውቁ ወረራ የማድረግ ህግን መቋጨት!’ የሚል አዲስ ህግ አርቅቃለች። ህጉ በፍጥነት ወረራ ማድረግን ጨምሮ ሳያንኳኩ ቤትን ወይም ንብረትን እንዲወሩና እንዲፈትሹ የሚፈቅደው ህግ በማታ ስራ ላይ እንዳይውል ሊከለክል ይችላል። ከሁለት አመት በፊት ብሬኦና ቴይለር በተመሳሳይ ምክንያት ህይወቷን ስታጣ ሳያንኳኩ ቤትን የመውረር ህግ እንዲሰረዝ የሚፈልጉ አያሌ ድምጾች ተስተጋብተው ነበር። ኢልሃንም ይህንን ድምጽ ህግ ሆኖ ወደ ተግባር እንዲቀየር አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች።
ብሬኦና ህይወቷ ካለፈ ከአጭር ጊዜ በኋላ ኮንግረስማን ራንድ ፓኡል ፍትህ ለብሬኦና የሚል ህግ አርቅቆ ነበር። በ ሉዊዝቬል ኬንታኪ በዚህ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አስገራሚ በሆነ ደረጃ ቀንሷል። የኬንታኪ ማእከላዊ የምርመራ መረጃ እንደሚጠቁመው በ ሉዊዝቬል ያሉ ፖሊሶች በ አስራ አራት ወራት ውስጥ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ለአራት ጊዜ ብቻ ሳያንኳኩ ወረራ አድርገዋል።
የጆርጅ እና ብሬኦናን ግድያን ተከትሎ በህዳር 2020 የሚኒያፖሊስ የ ፖሊስ ክፍል ሳያንኳኩ ወረራ ማድረግ ላይ የተወሰነ እገዳ የሚጥሉ ማሻሻያዎችን አውጥቷል። በግዜው የ ፖሊስ ክፍሉ በአመት 139 ሳያንኳኩ ተጠርጣሪን የመውረር ስራዎች እንደተሰሩ ገልጿል። ማሻሻያው ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በዘጠኝ ወራት 90 የሚሆኑ ሳያንኳኩ የግለሰብ ቤት ውስጥ የመግባት ድርጊቶች ተፈጽመዋል። ከማሻሻያው በኋላ በታየው ውጤትም በርካታ የሚኒሶታ ማህበረሰቦች ደስተኛ አይደሉም። ታዲያ ኢልሃንም ይሄንን ለመቀየር ቆርጣ ተነስታለች።
ኢልሃን “ሳያንኳኩ ወረራ ማድረግ ከ ዘር እንዲሁም ጥቁር ቀለም ካላቸው ሰዎች ጋር የተቆራኘ ልዩነት ላይ የተመሰረተ ጥልቅ ታሪክ አለው። ይህም ሌላኛው ፖሊሶች የሰዎችን ክብር ለመሸርሸር ተግባር ላይ እያዋሉት ያለ ዘዴ ነው።” ብላለች።
ከ አሚር ህልፈት በኋላ የሚኒያፖሊስ ሀላፊ ጃኮብ ፍሬይ በሁለት የሀገሪቱ ሊቆች ሳያንኳኩ ወረራ ማድረግ ላይ ቀጣይ ምርመራዎች እስኪደረግ ድረስ ሳያንኳኩ ወረራ ማድረግን የሚያግድ ትእዛዝ አውጥተዋል። እስካሁን ድረስ የ አሚር ጉዳይ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።