የስልክ ጥሪዎች፣ የመለክት ልውውጦች እንዲሁም የቪዲዎ ጥሪዎች ሁሉም ነጻ ናቸው። በ ዋትስአፕ እኚህን ለማከናወን ምንም አይነት ገንዘብ ማውጣት አይጠበቅብዎትም። ታድያ ምንድነው ሚስጥሩ? አብዛኞቹ ሰዎች የዋትስአፕን መተግበርያ ወደ ስልካቸው ሲያወርዱ የሚከፍሉት ዋጋ ምን አልባትም ከተወሰኑ ገንዘቦች በላይ እንደሆነ አይገነዘቡም። በ 2014 ዋትስአፕን የግሉ ማድረግ የቻለው ፌስቡክ እየፈለገ ያለው የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ እንደክፍያ ሆኖ እንደሆነስ?
ቀደም ብሎ የካቲት 8 ይጀምር የነበረውን ዋትስአፕን መጠቀም እስከፈለጉ ድረስ በዋትስአፕ አዲስ ግላዊነት ፖሊሲ እንዲስማሙ እንደሚገደዱ ያወቁ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ሁከት በማስነሳታቸው ፌስቡክ በድጋሚ እንዲጀምር የታሰበበትን ቀን እንዲመለከት አድርጎታል። በመሆኑም ፖሊሲው የሚጀምርበት ቅን ወደ ግንቦት እንዲተላለፍ ተደርጓል።
ፌስቡክ ዋትስአፕን በ $16 ቢሊየን የገዛው ሲሆን፤ $4 ቢሊየን በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም $12 ቢሊየን ደግሞ በ ፌስቡክ አጋርነት የሚቆይ ነው። በተጨማሪም $5.3 ቢሊየን ለዋትስአፕ ሰራተኞች እንደ ካሳ የተሰጠ ነው። በአጠቃላይ ፌስቡክ $21.8 ቢሊየን ወጪ አድርጓል። ይህም የዋትስአፕን ዋጋ እና የሚጠቀሙበትን ሰዎች ብዛት ያሳያል። የፌስቡክ ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግም ይህን አጠራጣሪ ውሳኔ ከአስተዋዋቂዎች የሚመጣ ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ኪሱ ለማስገባት ሲል ለመወሰን ፍላጎት እንዳደረበት የማይካድ እውነት ነው ።
ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያዎች ዋትስአፕ ላይ ስለማይመጣላቸው ማስታወቂያ ሰሪዎች የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት አይችሉም። ይሁን እንጂ አሁን ፌስቡክ ዋትስአፕን የግሉ በማድረጉ የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲጠቀም ያስችለዋል። የአሳሽ መረጃ ፣ የሞባይል አውታመረብ፣ የሞባይል ኦፕሬተር እንዲሁም የ አይፒ አድራሻ አንደ ምሳሌነት የሚጠቀሱ ፌስቡክ ከዋትስአፕ የሚወስዳቸው የግለሰቡ መረጃዎች ናቸው። እነዚህንም መረጃዎች ከፌስቡክ ስለ ተጠቃሚዎች እንደ እቃ ግዢ ልምድ ካሉ መረጃዎች ጋር በማጣመር ለከፋይ አስተዋዋቂዎች መሸጥን ነው ኢላማው ያደረገው።
እውነት ፌስቡክ የህን ያህል እርቀት ይጓዛል ? አስቲ የማርክ ዙከርበርግን የተወሰኑ የቀድሞው ታሪኮች እንመልከት። ከፌስቡክ በፊት በ 2003 ዙከርበርግ “ፌስማሽ” የተሰኘ መተግበርያ ፈጠረ። የ ሀርቫርድ ክሪምሰን የተባለ ጋዜጣም የ ታዋቂው “አም አይ ሆት ኦር ኖት” የተባለ ድህረ ገጽ ስሪት ሲል ገልፆታል። በመሆኑም ዙከርበርግ የ ሀርቫርድ አመራር ቦርድ ጋር በመቅረብ የሰዎችን የግል መረጃ በመጠቀም፣ ደህንነታቸውን እንዲሁም የቅጂ መብትን በመጣስ ተከሷል።
ከአመት በኋላ ፌስቡክን ከአብሮ መስራቾቹ ክሪስ ሂውዝ፣ ደስቲን ማስካቬስት እና ኤድዋርዶ ሳቨረን ጋር በመሆን ፈጥሯል። ፌስቡክን ከጀመረ በኋላ ፌስቡክ ለመጠቀም የሚያስገቡትን መረጃ ተጠቅሞ የሁለት ክሪምሰን ጋዜጠኞችን የኢሜይል መለያ ጠልፏል።
21 አመት ሳይሞላው የሰራቸው ስህተቶች ምን አልባትም ሊታለፍ ይችል ይሆናል ነገር ግን ዙከርበርግ ከ 15 አመት በኋላ በ2019 በድጋሚ ወደ ፌደራል ንግድ ኮሚሽን በመጠራት ክስ ቀርቦበታል። ፌስቡክ የፌደራል ንግድ ኮሚሽንን የ2012 ትእዛዝ በመተላለፍ ስለተጠቃሚዎች የግል መረጃና ደህንነት በመዋሸት በተጨማሪም በምን ያህል ደረጃ የሰዎችን የግል መረጃ እንደሚጠቀም የተሳሳተ መረጃ በመስጠት በታሪክ ትልቅ የተባለውን የ$5ቢሊየን የገንዘብ ቅጣት ተቆጥቷል።
የ5ቢሊየን ዶላር ቅጣት በሰዎች የግል መረጃዎች ጣልቃ ገብነትን ለማስወገድ በቂ ይሆናል? ለዙከርበርግና አብረውት ላሉት ይሄ በቂ አይሆንም። ለዚህም ይመስላል በዙከርበርግ እርምጃ የተደመሙ ሰዎች የዋትስአፕ ተቀናቃኝ ወደሆኑ መተግበርያዎች እያመሩ የሚገኙት። ዋትስአፕ በ ዩናይትድ እስቴት እና በ ዩናይትድ ኪንግደም በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል:: በዚሁ አመት ጥር መጀመርያ ላይ ዋትስአፕ በትልቁ ከሚወርዱ መተግበርያዎች ውስጥ አንዱ በመሆን ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ጥር አጋማሽ ላይ ወደ 23ተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል፡፡ ይህም ለዋትስአፕ “ዋትስአፕ ግላዊነትን ያከብራል እንዲሁም ይጠብቃል፡፡” ሲል ለማወጁ ምክያት ይሆናል፡፡ ሳይዘገይ ግን አልቀረም።
የቴሌግራም መስራች ፓኡል ዱሮፍ እንደተናገረው “ጥር ላይ በመጀመርያው ሳምንት ቴሌግራም ከ500 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ተጠቃሚዎችን አግኝቷል።” በማስከተልም “ከዛ በኋላም የተጠቃሚው ቁጥር መጨመሩን ቀጠለ እናም በመጨረሻዎቹ 72 ሰአታት ብቻ 25ሚሊዮን ሰዎች ቴሌግራምን ተቀላቅለዋል።” በ2020 በቀን ከነበረው አማካይ 1.5 ሚሊዮን አዲስ ተጠቃሚዎች ጋር ሲነፃፀር እጅግ የላቀ ለውጥ መሆኑን ገልጿል። “ከዚህ ቀደም ለሰባት አመታት ያህል የቴሌግራም መተግበርያን የሚያወርዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም የዚህ ግዜው ግን የተለየ ነው።” ሲል አክሏል።
በተገላቢጦሽ ደ’ሞ በጥር መጀመርያ ከ1,000 በዋናነት ከሚወርዱ መተግበርያዎች ውስጥ እንኳን ያልነበረ ‘ሲግናል’ የተባለ መተግበርያ ወደ አንደኛ ደረጃ መጥቷል፡፡ በተጨማሪም ዋትስአፕ ላይ የተፈጠረውነን ሁካታ ተከትሎ ቴሌግራም የአንዳንድ ሀገራትን ፕሬዝዳንት ቀልብ መሳቡ አልቀረም።የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮ እንዲሁም የቱርኩ ፕሬዝዳንት ታዪብ ኤርዶጋን ቴሌግራምን ተቀላቅለዋል። የበርካቶቹን ዋትስአፕን እየተዉ ወደ ተቀናቃኝ መተግበርያዎች ማምራት “በሰው ልጅ ታሪክ ትልቁ የዲጂታል ስደት ምስክሮች ነን።” ሲል ዱሮፎ አጠቃሏል።
ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ምን አልባትም ተጠቃሚዎች ዋትስአፕ የነሱን የግል መረጃ እንደሚጠብቅና እንደሚያከብር ለማመን በመቸገራቸው ዋትስአፕን ለመተው ተገደዋል። የዋትሰአፕ ተወዳዳሪ መተግበርያዎች በምጥቀት ባለሉበት ሰአት ዋትስአፕ ከዙከርበርግ እንዲሁም ከባልደረባዎቹ ጋር በመሆን እንዴት ከገባበተት አዝዕቅት መውጣት እንዳለበትና እንዴት የሰዎችን እምነት በድጋሚ ማግኘት እንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል።