የሰሜን አሜሪካ የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ የኤርትራ እግር ኳስ ውድድር በኮቪድ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ዳግም ሊጀመር ነው። ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 26 በ ሴንት ሳን ሊአንድሮ ካሊፎርኒያ ቤይ ኤሪያ ላይ ይካሄዳል።
የእግር ኳስ ውድድሩ ከሁሉም የአሜሪካ ክፍሎች የተውጣጡ ቡድኖችን ያቀፈ ነው። ተወዳዳሪዎቹ በሰሜን ምዕራብ ሲያትል፣ በደቡብ አትላንታ፣ በቺካጎ በመካከለኛው ምዕራብ እንዲሁም በበርካታ አካባቢዎች በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በአጠቃላይ 20 ቡድኖች በውድድሩ የሚሳተፉ ይሆናሉ።
ከ 2015 ጀምሮ የሰሜን አሜሪካ የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ደስታ ጎልማሶቹ በከፍተኛ ብቃት ሲወዳደሩ የኛ ዋና ትኩረት ታዳጊዎቹ ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከ20 የ ጎልማሶች ቡድን በተጨማሪ ለወጣቶች ከ 12 በላይ የሆኑ ቡድኖች ይኖራሉ። የደስታ የ 8 አመት ልጅ ኖልም የእግር ኳስ ጫማውን አድርጎ ወደ እግር ኳስ ሜዳ መግባትን በጉጉት የሚጠብቀው ነገር ነው።
በኮቪድ ምክንያት የተቋረጠው ውድድር ለመጨረሻ ግዜ የተደረገው በ 2019 በሚኒሶታ ነበር። በውድድሩ መረብ የተሰኘ ከዴስ ሞይንስ አዮዋ የመጣው አዲስ ቡድን በአሸናፊነት ዘውዱን በማጥለቁ ሁሉንም አስገርሟል። በአንዳንድ ውስብስብ ምክንያት የተነሳ ከሲያትል ጋር የተደረገው የሻምፒዮና ጨዋታ ውድቅ ተደርጓል። በዚህም መረብ በራሱ ሜዳ ከሚኒሶታው ዴንዴን ጋር ተወዳድሮ አሸንፏል።
ኤፍሬም ለሆርን መፅሔት እንደተናገረው የአትላንታው ኤላ ኤሪ የዘንድሮውን ውድድር ለማሸነፍ በዝግጅት ላይ ነው። ኤላ ኤሪ በተደጋጋሚ በተደረጉ ውድድሮች ላይ ጥሎ ማለፍ ሳይችሉ ቀርትዋል። በ በ2015 አትላንታ ውድድሩን ስታስተናግድ በግማሽ ፍፃሜ ላይ በሚኒሶታ ተሸንፈዋል። በተጨማሪም በ 2016 በግማሽ ፍፃሜው በሳን ዲዬጎ ተሸንፈዋል። ምንም እንኳን ኤፍሬም እንደ አብዛኞቹ የቀድሞ ተጫዋቾች ጡረታ በመውጣቱ ምክንያት በዚህ አመት መጫወት ባይችልም አትላንታን ለሚወክሉ ወጣት ተጫዋቾች ድጋፉን እያሳየ ይገኛል።
ኤፍሬም “ውድድሩ በጣም ጠንካራ ነው። ከውድድሩ በፊት ለወራት መዘጋጀት አለብህ። በዚያ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች እስቴድየሙን ሞልተው ይመለከቱሃል። ስለዚህ እስከ መጨረሻው መጫወት ይኖርብሃል።” ብሏል።
ከውድድሩ አጓጊነት በተጨማሪ ኤፍሬም ከቀድሞ ጓደኞቹ ጋር መገናኘት፣ መጓዝ እንዲሁም ሳምንቱን ከስራ ራቅ ብሎ ማሳለፍ ያስደስተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ደስታም ይህ ዝግጅት ለቤተሰብ በተለይም ለወጣቶች አንድነት ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን አጽዕኖት ሰቶ ተናግሯል።
አቶ ደስታ ዝግጅቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ እንጂ ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ግንኙነት እንደሌለው ይናገራል። በስፖርት እና በሌሎች ባህላዊ ዝግጅቶች የጓደኝነት እና የአንድነት ስሜትን የሚፈጥር ዝግጅት ብቻ ነው ብለዋል። ደስታ ወጣቱ ባህላዊ ግንዛቤን በሚሰጡ ጤናማ ተግባራት እና ውድድሮች ላይ መሳተፉ ጥቅም አለው ብለዋል።
ደስታ “ልጆቹ አስተዳደጋቸውን እና ቅርሶቻቸውን እንዲያውቁ እንፈልጋለን።” ይላል። አስከትሎም “ይህን ማወቅ ለእነሱ አስፈላጊ ነው።” ብሏል።
ዝነኛው አለም ሰገት ኤፍሬምን መጋበዝ ወጣቱን ከባህላዊ ምስሎች ጋር ለማስተዋወቅ የሚያስችል ጥሩ ጅምር ነው። አለም ሰገት ከኤርትራ ታላላቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ነበር። በዚህ አመት የውድድር ዝግጅቱን ለመካፈል ከኤርትራ ወደ ካሊፎርኒያ በአውሮፕላን ይሳፈራል።
አለም ሰገድ ኤፍርኤም ከ1986 እስከ 2003 ለአዱሊስ ተጫውቷል። በተጨማሪም ከ1991-2001 ለኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል። ጡረታ ከወጣ በኋላ ከ2003-2015 የድሮ ቡድኑ አዱሊስ ዋና አሰልጣኝ ነበር። በመቀጠልም ከ2015 እስከ አሁን ድረስ የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ እያገለገለ ነው።
የ አለም ሰገድ እውቅና በዚህ ብቻ አያበቃም። በኤርትራ ብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ማበልፅግያ ኃላፊ ነው። በ 2019 ቡድኑን በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ውድድር ላይ ለፍፃሜ እንዲቀርብ በማድረግ ከዩጋንዳ ጋር ተገናኝቷል።
ደስታ “አለም ሰገድን በክብር እንግድነት ከመሀከላችን በማግኘታችን በጣም ደስ ብሎናል። እሱ ፈርጥ ነው።” ብሏል።
ደስታ በኤርትራ ውስጥ የቀድሞ የአለም ሰገድ ቡድን አጋር ነበር። በሰኔ 23 ደስታ እና የቀድሞ የቡድን አጋሮቹ በኦክላንድ በመሰባሰብ በኤርትራ ውስጥ ለሚኖሩ የቀድሞ የቡድን አጋሮቻቸው የሚሆን ገንዘብ በኤርትራ ስፖርት ቤተሰብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በኩል ያሰባስባሉ።
ዓመታዊው የእግር ኳስ ውድድሩ እ.ኤ.አ. በ1986 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በዚህ አመት ለ 35ተኛ ጊዜ የሚዘጋጅ ይሆናል። ዝግጅቱ ቅዳሜ ሀምሌ 2 ከፌዴሬሽኑ አመታዊ ክብረ በዓል ጋር ይጠናቀቃል።