Horn Magazine
Wednesday, May 14, 2025
  • Home
  • National
  • World
  • Finance
  • Community News
  • Education
  • Sports
  • Health
No Result
View All Result
  • Home
  • National
  • World
  • Finance
  • Community News
  • Education
  • Sports
  • Health
No Result
View All Result
Horn Magazine
No Result
View All Result

Home » የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ከ ህወሀት ጋር የተኩስ አቁም አወጀ!

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ከ ህወሀት ጋር የተኩስ አቁም አወጀ!

April 4, 2022
in ዓለም
1 min read
Ethiopian Government Declares Humanitarian Truce with Tigray - የኢትዮጵያ
ShareSharePin

መቋጫ ያጣው የኢትዮጲያ የእርስ በእርስ ጦርነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ከመንጠቁ ባሻገር በርካቶችን ለስደትና ለአካል ጉዳት ዳርጓል። ለሁለት ዓመታት ያህል የዘለቀውን የሀገሪቱን አለመረጋጋት ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን አፋጣኝ የተኩስ አቁም ውሳኔን አውጇል።

የተባበሩት መንግስታት ባወጣው ዘገባ ከህዳር 2020 ጀምሮ ከ5.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የትግራይ ህዝቦች ከውጪው አለም ታግደው ቆይተዋል። እገዳው ከውጪው አለም ጋር የሚደረግ ማነኛውም ግኑኝነት እና ወደሃገሪቱ የሚገባ የሰብአዊ እርዳታንም ይጨምራል።

የፌደራል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰውን የአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ ርዳታ ነጻ እና ቀላል ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ በመግለጫው አስታውቋል። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ኤጀንሲው በትግራይ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና በአጎራባች ክልሎች ከያዙት አካባቢዎች እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በሀገሪቱ ሰላም ለመፍጠር ብዙ ሙከራዎች  የተደረጉ ቢሆንም ተኩስ ለማቆም የተደረጉ ጥረቶች ፍሬ ሲያፈሩ አልታዩም። ነገር ግን አሁን የፌደራል መንግስት በዚህ የእርቅ ስምምነት ላይ የትግራይ ፍላጎት እንዲኖር የተቻለውን አድርጓል ። ህወሓት በትዊተር ገፁ ላይ በሰጠው ምላሽ ይህንን ጸብ ለማቆም ያለውን ዝግጁነት አሳይቷል። ይህም የፌደራል መንግስት ጦርነቱ እንዳቆመ ያረጋግጣል።

የፌደራል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በሚዲያ መግለጫ ላይ እንደተናገረው “የኢትዮጵያ መንግስት ይህ የእርቅ ስምምነት  ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሻሽል ተስፋ ያደርጋል” ብሏል። ኤጀንሲው በመቀጠል ይህ የእርቅ ስምምነት “ግጭቱን ለመፍታት መንገድ ይከፍታል” የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል።

ህወሓት እጅ ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው በመግለፅ፤ የፌደራል መንግስት ለሰላምና ለሰብአዊ እርዳታ ያለው ቁርጠኝነት ላይ ግን ስጋት እንዳለው ገልጿል። ህወሓት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃላቸውን ጠብቀው ወደ ትግራይ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ተጨባጭ የሆኑ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማሳሰቡን  ለ AFP በላከው መግለጫ አስታውቋል።

መንግስት ሰላም የማስፈን ፈቃደኝነቱን ለማሳየት ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ በየቀኑ የሚደረጉ የአውሮፕላን በረራዎችን መፍቀዱ ነው። ቱርክንና አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት በፈደራል መንግስቱ ሰላምን ለማምጣት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን አበረታተዋል። 

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ. ብሊንከን በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ያወጣውን ላልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እርቅ ማወጁን አሜሪካ በደስታ የተቀበለችህውና የምትደግፈው ነው” ብለዋል። አክለውም “ጦርነቱን የማቆም ቁርጠኝነት በትግራይ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች እና ለሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እና ማህበረሰቦች ሰብአዊ እርዳታን ለማስቀጠል ወሳኝ እርምጃ ሊሆን ይገባል።” ብለዋል።

ህወሓት የፌደራል መንግስት ቃሉን እንዲያከብር እየጠየቀ ሲሆን የፌደራል መንግስት ደግሞ በአፋር እና በትግራይ አዋሳኝ ቁልፍ ቦታዎች ላይ የሰፈሩት የትግራይ ተወላጅ ሃይሎች እንዲወጡ እየጠየቀ ይገኛል።  

ይሁን እንጂ ከነዚህ ሁለት ወገኖች በተጨምሪ ሰላምን ለማስፈን አስፈላጊ የሆኑ ሊሎች አካላት አሉ። በሁለቱ ወገኖች ብቻ የሚደረገው እርቅ ስኬታማ ቢሆን እንኳን ሰላም ለመፍጠር በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ያሉ ሌሎች አካላት አሁንም ጦርነቱን ለምቆም ዝግጁ ላይሆኑ ይችላሉ። 

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ውስጥ አሁንም የመንበረ ስልጣኑን መብት የሚጠይቅ መንግስት “ኦነግ ሻኔ” ብሎ የሰየመው ቡድን መኖሩ ይታወቃል። ለመዋጥ የሚጎመዝዘው ከህወሓት ጋር እርቅ የመፍጠር ጉዳይ የሁለት አመት ጦርነት መቋጫ ሊሆን ቢችልም የአዲስ ተቃዋሚዎች መጀመሪያ ሊሆን ይችላል። 

 

Related Posts

Dr. Tedros
ዓለም

አለም ከዩክሬን ጋር እያዘነ ባለበት ጊዜ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ሃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በ አፍሪካ ስላለው ግጭት መከሩ

April 25, 2022
rubel ሩብል
ዓለም

የራሺያ ሩብል የተለያዩ ማዕቀቦች ቢጣሉበትም በአጭር ግዜ አንሰራራ!

April 19, 2022
Israel Attempts to Ban Ethiopians for Easter እስራኤል
ዓለም

እስራኤል የኢትዮጲያውያን ጉዞ እግድ አነሳች!

April 15, 2022
Worldwide Mercenaries Seeking to Help Ukraine ዜሌኒስኪ
ዓለም

አለም አቀፍ ተከፋይ ጦረኞች ዩክሬንን ለማገዝ ፍቃደኝነታቸውን አሳዩ!

March 24, 2022
Russia Ukraine War threatens world food supply
ዓለም

የዩክሬን ጦርነት የአለም ምግብ አቅርቦት ላይ ስጋት ጣለ!

March 21, 2022
African Nations Divided on the Russia-Ukraine Crisis
ዓለም

አፍሪካውያን በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ላይ የተለያየ አቋም አሳዩ!

March 23, 2022

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

POPULAR POST

No Content Available
Load More

RECENT POST

Jamal Osman Seeks Minneapolis City Council Re-Election

Jamal Osman Seeks Minneapolis City Council Re-Election

March 8, 2023
Ethiopian

New Direct Flights from Atlanta to Ethiopia

January 25, 2023
Zaynab Mohamed Sworn into the Minnesota Senate

Zaynab Mohamed Sworn into the Minnesota Senate

January 6, 2023
Last African Nation Standing in the World Cup Falls to France

Last African Nation Standing in the World Cup Falls to France

December 19, 2022
Cameroon Defeats Brazil but Fail to Qualify for the Next Round

Cameroon Defeats Brazil but Fail to Qualify for the Next Round

December 13, 2022
Horn Magazine

The Horn Magazine is a U.S. based, online magazine that serves to provide meaningful articles on a variety of subjects that impact your daily lives.

Contact info@hornmagazine.com

CATEGORIES

English                Amharic                 Somali 
National                ብሔራዊ                    Qaran
World                     ዓለም                      Adduunka
Sports                    ስፖርት                   Ciyaaraha
Finance                  ፋይናንስ                 Maaliyadda
Health                    ጤና                       Caafimaadka
Education              ትምህርት                Waxbarasho
Entertainment      መዝናኛ                   Madadaalo

SUBSCRIBE NEWSLETTER

Loading
  • About
  • Advertise
  • Privacy & Policy
  • Contact

© 2021 Horn Magazine

No Result
View All Result
  • Home
  • National
  • World
  • Finance
  • Community News
  • Education
  • Sports
  • Health

© 2021 Horn Magazine