ከተመሰረተ ትንሽ ግዜ የሆነ የአትላንታው ኤላ ኤሪ ቡድን ሳን ፍራንሲስኮን በግዛቱ ካሊፎርኒያ በማሸነፍ ዋንጫውን መውሰድ ችሏል። ምንም እንክዋን ተጨዋቾቹ በጉዳት እና በቅጣት ከሜዳ ቢርቁም ያጋጠማቸውን ተቀናቃኝ ሁሉ ማሸነፍ ችለዋል። ውድድሩን 6 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል።
ኤላ ኤሪ በሩብ ፍጻሜ አሌክሳንድሪያን 2-0 ሲያሸንፉ በግማሽ ፍፃሜ አዮዋን 3-1 አሸንፏል። የፍፃሜ ጨዋታውን በጉጉት ሲጠብቁት የቆዩ ሲሆን በ 2019 በግማሽ ፍፃሜ ካሸነፋቸው የ ሳን ፍራንሲስኮው ዳህላክ ቡድን ጋር በሜዳቸው ተጫውተዋል።
“2019 ለእኛ የመጀመርያ አመታችን የነበረ ቢሆንም ጥሩ ተጫውተናል። በውድድሩ ከባድ የነበረውን የዳላስ ቡድን አሸንፈናል። ለ ሳን ፍራንሲስኮው ዳህላክ ቡድንም ዝግጁ ነበርን።” ሲሉ የኤላ ኤሪ አሰልጣኝ ዴሳል ተናግረዋል። በመጀመርያው አጋማሽ አትላንታ 3-0 እየተመራ ነበር። ይሁን እንጂ በ ሁለተኛው አጋማሽ ብቃቱን አጠናክሮ 5 ጎሎችን በማስቆጠር የደቡብ ምርጥ ቡድን መሆናቸውን ከማሳየት ባሻገር ዳላስን አስደንግጧል። በዚህ አመት ደግሞ የበለጠ ተሻሽለው በመምጣት እና በተከታታይ ሁለት ወራት በመሰልጠን የሀገሪቱ ምርጥ ቡድን መሆኑን አስመስክሯል።
አትላንታ ወደ ፍጻሜ ጨዋታው እያመራ ሲሄድ ሙሉ ተጫዋቾችን ይዞ አልነበረም። በግማሽ ፍጻሜው ከ አዮዋ ጋር ባደረገው ጨዋታ ረዳት አምበሉ አወት በጉዳት ምክንያት ለቀሪ ጨዋታዎች ተሳታፊ ሳይሆን ቀርቷል። በተጨማሪም በአሌክሳንድሪያ የሩብ ፍፃሜው ቢጫ ካርድ ያገኘው ኤፍሬም በአዮዋ ላይ ሌላ ቢጫ ካርድ በማግኘቱ ከውድድሩ ተሰናብቷል።
ይሁን እንጂ የአትላንታ ተከላካዮች የ አዮዋ ተጫዋቾች ምንም አይነት ግብ እንዳያስቆጥሩ መከላከል ችለዋል። “አብዛኞቹ ተከላካይ ተጫዋቾቻችን በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።” ሲል የቡድኑ አምበል ተናግሯል። አስከትሎም “እኛ ምናልባትም በውድድሩ በእድሜ ትንሾቹ ቡድን ነበርን።” ብሏል።
በላንድሪ እና ሀፍታም ሁለት ግቦች አትላንታ 3-1 በማሸነፍ አጠናቋል። በስተመጨረሻም የፍጻሜ ውድድሩ በ ሳን ፍራንሲስኮ ሜዳ ከሳን ፍራንሲስኮ ቡድን ጋር ነበር። የ ኤላ ኤሪ አሰልጣኝ “ምላሽ የምንሰጥበት ጊዜ ነበር።” ብለዋል። አስከትለውም በሁለት ቢጫ ካርድ የተሰናበተው የቡድኑ ተጫዋች ኤፍርኤም ባይኖርም ማሸነፍ ግድ ነበር ብለዋል።
የ ሻምፒዮና ጨዋታው ሲጀመር የቅዝቃዜው መጠን ወደ 61 ከፍ ማለቱ የአየር ሁኔታውን ለለመዱት የ ሳን ፍራንሲስኮ ተጫዋጮች ምቹ የነበረ ሲሆን በሙቀት ሲጫወቱ ለቆዩት የ አትላንታ ቡድኖች አስቸጋሪ ነበር።
ሁነቶቹ ከዚህ በተቃርኖ የቆሙም ይመስሉ ነበር። በመጀመርያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ጎል አስቆጥረዋል። ሳን ፍራንሲስኮ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር በተዳከሙት አትላንታዎች ላይ መጠነኛ መነቃቃትን ፈጠሩ። ነገር ግን የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃ ሲቀረው ከላንድሪ ወደ ቤቴል ከዝያም ወደ ደሳሌ የተሻገረችው ኳስ ወደ ጎል ተቀይራ አቻ አድርጋቸዋለች። ይህም ለአትላንታ በሁለተኛው አጋማሽ ጎል እንዲያስቆጥር መነቃቃትን ፈጥሯል።
ጨዋታው 45 ደቂቃ ሲቀረው ያለ ምንም ተቀያሪ እየተጫወቱ ለነበሩት 11 የ አትላንታ ተጫዋቾች ፈተናው ከባድ ነበር። ሳን ፍራንሲስኮ በበኩሉ 15 ተጫዋቾች እና ሞራል የሚሰጣቸው ደጋፊ ነበራቸው።
አትላንታ እንደገና መሰባሰብ እና ዳግም መነቃቃት ነበረበት። አምበስ “ልንሰራ የመጣነውን እናውቅ ነበር። እርሱን ለማሳካት ደግሞ ልምድ አለን።” ብሏል።
በአዮዋ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ የአትላንታ ወጣት ተከላካይ ተጫዋቾች በሁለተኛው አጋማሽ ሳን ፍራንሲስኮ ምንም ነጥብ ሳያስቆጥር እንዲወጣ አድርጎታል። ቤቴል በሁለተኛው አጋማሽ ጎል በማስቆጠር አትላንታ 2-1 እንዲመራ ሲያደርግ ዴሳል በበኩሉ ፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር ልዩነቱን በ 3-1 አስፍቶ ሳን ፍራንሲስኮ በመጨረሻ ሰአት ላይ ውጤቱን መቀልበስ እንዳይችል አድርጓታል።
በውድድሩ በተሳተፈበት ሁለተኛ አመት የአትላንታው ኤላ ኢሪ ከተሳታፊነት ከፍ ብሎ አይበገሬ መሆኑን አስመስክሯል። በወጣቶች የተዋቀረው ይህ ቡድን አሁንም በዚህ ድል አልረካም አምበስ “ቀጣይ አመት ዳግም ለማሸነፍ እንመለሳለን።” ብሏል።