በአሜሪካ ታሪክ ከ ስፓኒሽ ፍሉ በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኮቪድ 10 ሚሊየኖችን ገሏል።ይህ ወረርሽኝ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከሌሎቹ በበለጠ ሰለባ አድርጓቸዋል። ታድያ በዋነኝነት የተጎዱት የመህበረሰቡ ክፍሎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ናቸው።
የድሀ ህዝቦች የወረርሽኝ ሪፖርት በ ድህነት፣ በዘር እና በኮቪድ-19 መሀከል ያለውን ቁርኝት ባሳየበት ጥናት እንደተመላከትው ድሆች በሚበዙባቸው ክልሎች የሚኖሩ አሜሪካውያን በሀብታም ክልሎች ውስጥ ከሚኖሩ አሜሪካውያን በሁለት በእጥፍ እየሞቱ ነው።
የኮቪድ ዝርያዎች እየበዙ እና እየተለዋወጡ በመጡ ቁጥርቁጥር ደግሞ ነገሩን አስከፊ አድርጎታል። በኦሚክሮን ዝርያ ድሀዎች በሚበዙባቸው አውራጃዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሀብታሞች ካሉባቸው አውራጃዎች ከሞቱት ሰዎች በ ሶስት እጥፍ ሲበልጥ በ ዴልታ ዝርያ ደግሞ በአምስት እጥፍ ይበልጣል።
ጥናቱ በድሀ ክልሎች ውስጥ እንደዚ ላለው ከፍ ያለ የሞት መጠን መፈጠር መንስኤዎችን መርምሯል። ሪፖርቱ ሀብታም እና ድሃ ክልሎችን በማነፃፀር በነዚህ ክልሎች መካከል በሚሰጠው የጤና አገልግሎት ደረጃ ላይ ያለውን ከፍተኛ ልዩነት አሳይቷል።
ለሪፖርቱ ቁልፍ አስተዋፅኦ ያበረከተው የዝቅተኛ ገቢ ያልቸው ህዝቦች ዘመቻ ሊቀመንበር ዊልያም ባርበር ግኝቶቹ “ቸልተኝነትን እና አንዳንዴም ሆን ተብሎ በድሆች ላይ ላለማተኮር የሚደረጉ ውሳኔዎችን ግልጽ አድርጓል።” ብለዋል። አክለውም “ኮቪድ -19 በድሆች እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ማህበረሰቦች ላይ የሚያሳድረውን ጉዳት የሚያሳይ ምንም አይነት ስልታዊ ግምገማ የለም።” ብለዋል።
ተመራማሪዎቹ እንደ የ ኮቪድ ሞት፣ ድህነት፣ ዘር፣ ስራ አጥነት እና የፖሊስ ጥቃትን የመሳሰሉ በክልል ደረጃ ላይ ያሉ መረጃዎችን ገምግመዋል። ተመራማሪዎች በእነዚህ ክልልሎች ውስጥ የዘር መረጃ አለመኖሩ የሀብት ምደባው በጣም በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች በተመጣጠነ መልኩ ተደራሽነት እንዳይኖር አድርጓል ብለው ያምናሉ።
የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች አውታረ መረብ ከፍተኛ የምርምር ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አላይና ሊንች “በዚህ ዘገባ ላይ መናገር የማንችለው ነገር የሞቱት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ነው” ብለዋል። ነገር ግን “እኛ ማለት የምንችለው የድሃው አውራጃዎች ሀብታ ከሆኑት አውራጃዎች የሚበልጥ ሞት መመዝገቡ ሀዘኑንም እጥፍ እንዲሆን አድርጎታል።” ብለዋል።
በጥናቱ ውስጥ ከ 3,200 በላይ የአሜሪካ አውራጃዎች መረጃ ተሰብስቧል። ከ 3,200 አውራጃዎች መካከል በጣም ድሆች የሆኑት 300 አውራጃዎች ከፍተኛውን የሞት ደረጃ ይይዛሉ። በእነዚያ አውራጃዎች ውስጥ 45% የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች ነው። አመታዊ መካከለኛ ገቢያቸው 20,000 ዶላር ሲሆን በአውራጃው ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች የተለያየ ዘር ያላቸው ናቸው።
ባርበር “በዚህች ሀገር ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ድሆች እና ዝቅተኛ ሀብት ያላቸው ሰዎች ችላ መባላቸው እና በተለይም ይህንን ጥቂቶች ካገኙት በትሪሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች አንፃር ስንመለከተው ሥነ ምግባር የጎደለው፣ አስደንጋጭ እና ኢፍትሃዊ ነው።” ብለዋል።
በኮሎምቢያ ፕሮፌሰር የሆኑት ጄፍሪ ሳችስ ሪፖርቱ በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያለውን ክፍተት ያሳያል ብለዋል። “ሞትን፣ መታመምን እንዲሁም ወጪዎችን በተመለከተ የወረርሽኙ ሸክም ድሆች፣ ሴቶች፣ እና ነጭ ያልሆኑ ሰዎች ላይ ያመዝናል” ብለዋል።አስከትለውም “ድሆች የአሜሪካ ወሳኝ ሰራተኞች ናቸው። በግንባር ቀደምትነት ህይወትን የማዳን ስራ ይሰራሉ። ሆኖም የበሽታና የሞት ተጠቂ የሆኑትም እነሱ ናቸው።” ብለዋል።
በ ሰኔ 18 የዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ህዝቦች ዘመቻ አባላት ከ ቀሳውስት እና ከማህበራት መሪዎች ጋር በዋሺንግተን ባደረጉት ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ባርበር ያለምንም ማወላወል በቀጥታ “በዚህች በአለም ታሪክ ሀብታም በሆነችው ሀገር ያለው የድህነት እና የስግብግብነት ደረጃ የማራል ቀውስን እና የስግብግብነት ፖለቲካ ውድቀትን በውስጡ የያዘ ነው።” ብለዋል።
ይህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ህዝቦች ዘመቻ በ 1960 ትኩረቱን ለድሆች ኢኮኖሚያዊ ፍትህ እንዲሰፍን ትግል በማድረግ የጀመረው በደቡብ ክርስትያናዊ አመራር ኮንፍረን ሲሆን ዋና አስተባበሪውም ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ነበር።
በአሁኑ ግዜ ዘመቻው በ ባርበር መሪነት ስር ሲሆን ቄስ ሊዝ ቴዎሃሪስ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ይመሩታል። ይህ ንቅናቄ የስደተኞች ማሻሻያ፣ የሰራተኛ መብት፣ የመኖሪያ ቤት እኩልነት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ያካትታል። በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ በጣም ድሀ አውራጃዎች ለተከሰቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ሞት ይህ ዘመቻ በትኩረት በመነጋገር ግንባር ቀደም ሆኖ ቆይቷል።