የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ እንዲሁም ከአትላንታ ወደ ኢትዮጵያ ቀጥታ በረራ ሊጀምር በመሆኑ ከዚህ በፊት እንደነበረው ከ አትላንታ ወደ ኢትዮጵያ ወይም ወደ የትኛውም የአጎራባች ሀገራት ስትጓዙ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ዘለግ ያሉ ጊዜያትን ማጥፋት አይጥበቅብዎትም።
አገልግሎቱ ግንቦት 16 የሚጀመር ሲሆን በሳምንት አራት ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ አትላንታ በረራ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አትላንታ ከመድረሱ በፊት በ ዱብሊን ከተማ የተወሰነ የሚቆም ይሆናል።
ዋና ስራ አስኪያጅ ባልራም ብሄኦዳሪ “የዓለማችን በጣም የተጨናነቀ እና ቀልጣፋ አየር ማረፊያ እንደመሆናችን መጠን የእኛ ተልእኮ ማህበረሰባችንን ከአለም ጋር በማገናኘት የላቀ ስራ መስራት ነው።” ብለዋል። አክለውም “የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ አትላንታ የሚያደርገውን በረራ ስንቀበል በጣም ደስ ብሎናል” ብለዋል።
ቀጥታ የበረራ አገልግሎቱ የአትላንታ ነዋሪዎችንም አስደስቷል። ሶፊያ መልካሙ “ከአትላንታ ወደ ዲሲ ከጠዋቱ 11 ሰአት በረራ አድርገን ከዚያም ለአምስት ሰአታት ያህል ቀጣዩን በረራ ለማድረግ መጠበቅ አሰልቺ ነበር። ከአትላንታ በቀጥታ በረራ ማድረግ ድካሙን ቀላል ያደርገዋል።” ስትል ተናግራለች።
ሌላው ሶፊያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየወሰደችው ያለው አማራጭ ከአትላንታ ወደ ቱርክ አየር መንገድ ቀጥታ በረራ ማድረግ ነው። ግን የዚህ ችግር “በኢስታንቡል ውስጥ ሌላ ረጅም ጊዜ መጠበቅ ነው።” ትላለች።
የአትላንታ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስም ስለ አየር መንገዱ አዲስ አገልግሎት ያለውን ደስታ ገልጿል። ዲከንስ “የአየር አገልግሎታችንን ወደ አፍሪካ ለማዳበር እና ለማስፋፋት እየሰራን በመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ‘ሀርትስፊልድ-ጃክሰን’ የሚያደርገው አዲስ በረራ ለከተማችን ሌላ ድል ነው።” ብለዋል። “የአትላንታን እና የአዲስ አበባን የበለፀጉ እና ተለዋዋጭ ከተሞችን አዲስ ግንኙነት ስናከብር በኢትዮጵያ ካሉት አጋሮቻችን ጋር ጠንካራ እና የተሳካ አጋርነት እንደምንፈጥር እንጠብቃለን።” ብልዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አትላንታን ከቺካጎ፣ በ ኒውጀርሲ ከሚገኘው ኒውዮርክ አየር ማረፍያ፣ ኒውዮርክ እና ዋሽንግተን ዲሲ በመቀጠል በአሜሪካ 5ኛ መዳረሻ ከተማ አድርጎታል። እነዚህ ከተሞች ለመካከለኛው ምዕራብ ቺካጎ በጣም ቅርብ ከተማ ስለሆኑ በምእራብ የባህር ዳርቻ ላሉ ነዋሪዎች ያን ያህል ምቹ ላይሆኑ ይችላሉ።
ነገር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለ እና ከ70 አመታት በላይ እየሰራ ያለ አየር መንገድ እንደመሆኑ መጠን በቅርብ ግዜ ውስጥ በምዕራቡ ዓለም አዲስ የመዳረሻ ማዕከል ይኖረው ይሁን ማን ያውቃል። አየር መንገዱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በስካይትራክስ ‘ምርጥ አየር መንገድ’ ሽልማትን ያገኘ ሲሆን ከ2011 ጀምሮ የስታር አሊያንስ አባል ነው።