ከ ኮቪድ 19 አገግመን ወደ ድሮ የህይወት መስመራችን መመለስ ስንጀምር ዳግም ነገሮችን እንድናስተካክል ያስገደደን አዲስ የኮቪድ 19 ዝርያ አሚክሮን መቷል። ይህ አዲስ ዝርያ የእለት ተእለት እንቅስቃስያችንን እንድናስተካክል በማድረግ ብቻ አልተገታም! ይልቅስ ምጣኔ ሀብታችን ላይ ክፍተት በመፍጠር በድጋሚ የ ገንዘብ እንቅስቃስያችንን እንድንመለከት አስገድዶናል።
በኦሚክሮን ዝርያ አስገዳጅነት የተለያዩ የስራ ዘርፍፎች ተጎድተዋል። ከብዙዎቹ መሀከል አየር መንገዶች በአዲሱ የኮቪድ 19 ዝርያ የተያዙ ሰዎች በመበራከታቸው በሺህ የሚቆጠሩ በረራዎችን መሰረዛቸው እንዲሁም ሬስቶራንቶች በድጋሚ የስራ ሰአታቸውን እንዲቀንሱ መገደዳቸው የሚጠቀስ ነው። ኦፕን ቴብል የተሰኘ የሬስቶራንቶች ቅድምያ ቦታ ማያስያዥያ ተቋም እንደገለፀው ከሆነ በ ዲሴምበር 2021 የመጨረሻ ሳምንታት የሬስቶራንት ተጠቃሚዎች ቁጥር በ ተመሳሳይ ግዜ በ2020 ከነበረው አንፃር በ 10% ቀንሷል።
ይሁን እንጂ የሙዲ አናሊቲክስ መሪ የሆነው ማርክ ዛንዲ ዛሬም ቢሆን በተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ክፍተት ላይ ተስፋ አለው። ለአጭር ግዜ ይላል ዛንዲ “በአዲሱ ዝርያ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ይጎዳል። ከመጀመርያው የበሽታው ሞገድ ተጨማሪ ሰዎች ይጎዳሉ ቢሆንም በትንሽ ግዜ ውስጥ ይህ ያልፋል። አሚክሮን የሰዎችን ባህሪ እና የቢዝነስ ስርአት ቀይሮታል።” በማለት የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚዎች ቁጥር መመናመኑን ያወሳል። ይህን ሀሳብ ሮይተርስ “እንደ ፌደራል ሪስርቭ መረጃ ከሆነ የ ክሬዲት ካርድ ተጠቃሚዎች በዲሴምበር 8 አነስተኛ ነበር። ይህም ከ ኦክቶቨር ጀምሮ በየሳምንቱ ይጨምር ከነበረው ተቃራኒ ነው።” ሲል አስተጋብቶታል።
የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚዎች ቁጥር ዝቅ ከማለቱ እና ሌሎች የስራ ዘርፎችም ችግር ላይ ቢሆኑም ዛንዲ ይህ በቅርብ ግዜ እንደሚወገድ ያምናል። ከመጀመርያው የኮቪድ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያላንሰራራው የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት እንደ ዛንዲ እምነት ከሆነ በ መጀመርያዎቹ 2022 ወራት በ 2% ያገግማል።
ይሁን እንጂ ከ ዛንዲ ሀሳብ በተቃራኒ የቆሙም አሉ። የ ፌዴራል ሪዘርቭ ሀላፊ የሆነው ጄሮም ፖውል “አዲሱ የኮቪድ 19 ዝርያ የተቀጣሪዎችን ቁጥር በመቀነስ እና ሎሎችንም የስራ ዘርፎች በመጉዳቱ ተጨማሪ የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት ሰበብ ሆናል።” ይላል። ይህ ሀሳብ ለ ሁለተኛ ግዜ ለተቋሙ ሀላፊነት ሲመረጥ ለምጣኔ ሀብት እድገት ያለውን ተስፋ እና ከአመታት ኋላ የሚከሰት ትልቁ እድገት ይሆናል በማለት ከተናገረው ሀሳብ ጋር የተቃረነ ነው።
እንደ ኦክክስፎርድ ትንበያ ከሆነ ለቀጣይ አመት በ 4.4% ከፍ ይላል ተብሎ የነበረው ኢኮኖሚያዊ እድገት በኦሚክሮን የተነሳ ዝቅ ብሎ በ 4.1% ተገቷል። የጄፍሪስ ስነምጣኔ ባለሙያዋ ቶማስ ሲሞንስ “ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በ ጃንዋሪ ይቀዘቅዛሉ። ይህ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የሰራ ቅጥር እና ሎሎች እንቅስቃሴዎች ልክ እንደ ዲሴምበር 202 በቀጣዮቹ ወራት እንደሚቀዛቀዙ ይገመታል።” ስትል ተናግራለች።
ይህን የአሚክሮን ችግር ለመፍታት የባይደን አስተዳደር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው። በዛ ያሉ ክትባቶችን፣ ምርመራዎችን እና በየቤቱ አፋጣኝ ምርመራዎችን አዘጋጅቷል። የ አሜሪካ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በአማካይ 4 የኮቪድ ምርመራዎችን በየቤቱ ልኳል በተጨማሪም ባይደን የተማሪዎችን ብድር ክፍያ እስከ ሜይ 1/2022 አራዝሟል።
ይህ ብቻውን የሀገሪትዋን ምጣኔ ሀብት ለማነቃቃት በቂ ነው? የሚለው ጥያቄ ግን ተጨማሪ መልስ ያሻዋል። እንደ ምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዛንዲ ተስፋ ከሆነ በ 2022 የሀገሪትዋ ምጣኔ ሀብት በ 4% ያንሰራራል። ሮይተርስ ይንን “ይህ ከወረርሽኙ በስተፊት በነበረው አስር አመታት ሲነቃቃ የነበረውን የምጣኔ ሀብት እድገት በ እጥፍ እንደሚጨምረው ይገመታል።” ሲል ዘግቦታል።