ባለፉት ጥቂት አመታት በአሜሪካ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ጥቃት መንስኤ የእስልምና ጥላቻ ነው። ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በምእራብ ዋሽንግተን ብቻ በተለያዩ የእስልምና ማዕከላት ላይ ሶስት ጥቃቶች ተፈጽመዋል። እንዲሁም በመጋቢት መጀመርያ ላይ አራተኛው ጥቃት በ ዋሽንግተን ከሲያትል በስተደቡብ 15 ደቂቃ ተጉዞ በሚገኘው በቡሪን የአሜሪካ ወጣት ሙስሊሞች ፋውንዴሽን ማእከል ላይ ሌላ ጥቃት ደርሷል።
የማዕከሉ ኢማም የሆነው ዶ/ር የህያ ሱፊ እንደገለጸው መጋቢት 7 ከቀኑ 9 ሰአት በማዕከሉ ውስጥ እንዳለ ከፍተኛ የግጭት ድምጽ መስማቱን አሳውቋል። ወደ ቦታው ሲደርስም የተሰባበረ መስታወት ማየቱን ተናግረዋል። አንድ ሰው መኪናውን ከህንጻው ጎን አጋጭቶ ሲሸሽ የተሰባበረ የመኪና ስባሪ መቅረቱንም አስተውሏል።
የህያ “እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ይሀንን ክስተት ትኩረት ሰጥተን ነው የምናየው። በተሽከርካሪው የተመታው ቦታ ብቸኛው የአሜሪካ ወጣት ሙስሊሞች ተቋም የአምልኮ ስፍራ ነው። በግዜው ሰዎች እዚያ ቦታ ላይ የስግደት ስነ-ስርአት እየፈጸሙ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ብሎም የህይወት መጥፋት ሊያስከትል ይችል ነበር።” ብሏል።
በ2021 መገባደጃ ላይ ከአሜሪካ ወጣት ሙስሊሞች ተቋም ብዙም ሳይርቅ ታኮማ በተባለ እስላማዊ ማእከል ላይ እሳት ተነስቷል። በተጨማሪም በብዛት የካምቦዲያ ማህበረሰብ ተወላጆች በሚገኙበት አካባቢ በዋሽንግተን የኦሎምፒያ እስላማዊ ማዕከል ላይ ፈንጂ ተወርውሯል። ልክ እንደዚሁ በ ማውንትሌክ ቴሬስ ኡመር አል-ፋሩቅ የተባለ መስጂድ ሊወድም ችሏል። በተከታታይ የደረሱ እነዚህ ጥቃቶች በሙስሊሞች ላይ መፈፀማቸው ድርጊቲ እንዲሁ በአጋጣሚ ነው የተከሰተው ብሎ ለማሰብ አስችጋሪ ያደርገዋል።
እንደ እድል ሆኖ ማእከሉ የተተንቀሳቃሽ ምስል መከታተያ መሳርያ ስለነበረው ፖሊስ ጉዳዩን በምስሉ እየታገዘ እየመረመረ ይገኛል። ጥቃቱን ያደረሰው አካል ብራማ ቀለም ያለውን ቶዮታ ኮሮላ መኪና እየነዳ አከባቢው ላይ ታይቷል። የህያ “ክስተቱ ድንገተኛ አልነበረም” ይላል። ወንጀለኛው ወደ ፓርኪንግ ቦታው ለመሄድ ከብረት ሰንሰለቱ በታች መኪናውን አሽከርክሯል። ከዚያም ወደ ጸሎት ቦታው በመንዳት መኪናውን አጋጭቶ በደቂቃዎች ውስጥ በፍጥነት ሄዷል ።
በቀጣዩ ቀን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ከሌሎች ማህበረሰቦች እና የሌላ እምነት ተከታዮች ጎን ለጎን በመሆን አብሮነቸውን አሳይተዋል። የቡሬን ፖሊስ አዛዥ ቴድ ቦይን ጨምሮ በፌደራል፣ በክልል እና በከተማ ደረጃ የህግ አስከባሪ አካላት እና የተመረጡ ባለስልጣናት የጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል። አንድ ላይ በመሆን በአምልኮ ስፍራዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማውገዝ “ከሙስሊም ጎረቤቶቻችን ጎን እንቆማለን!” የሚል መፈክር ይዘው ተገኝተዋል።
ከተከፈተ አንድ አመት ባልሞላው ማእከል ውስት በተፈጠረው ክስተት የሙስሊሙ ህብረተሰብ አባላት እጅጉን ተደናግጠዋል። የተፈጠረው የጥላቻ ድርጊት ከመጀመርያው ጊዜ ጀምሮ ከማህበረሰቡ ጋር ለነበረችው የ21 አመቷ የዋሽንግተን ተወላጅ አህላም ኑር እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነበር። አህላም “ዜናውን ስሰማ በጣም አዝኛለው። መአከሉ ሲመረቅ እያስተናገድን የነበርንበትን ቀን አስታውሳለሁ።” ብላለች።
አህላም እና ቤተሰቦቿ ለማእከሉ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ እንዲሁም ባለፈው አመት በአሜሪካ ሙስሊም ወጣቶች ማእከል ታላቅ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል። አህላም በመጀመሪያው የኢድ ሰላት ላይ መስጅዱን በማስዋብ ድርሻዋን ተወታለች። አህላም “ማናችንም ብንሆን የሆነ ግለሰብ ወደ እምነት ቦታችን አመጽን አልሞ መኪና እየነዳ ይመጣል ከዛም ለመሸሽ ይሞክራል ብለን ልናስብ አንችልም”። በማዕከሉ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ነገር ነው። ሁላችንም ልብ የሚኖር ይሆናል።” ትላለች።
ሌላዋ የማህበረሰቡ አባል የሆነችው ዘይነብም ጥቃቱ ሀሳብዋን ይዞት ቆይቷል። ማዕከሉ “ደህንነት እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ እና አእምሮዬን ከተለያዩ ሃሳቦች የማጸዳበት ቦታ ነው። ለሁላችንም ሰላም የሚሰጠን ቦታ ሊያበላሽ የሚፈልግ ሰው አለ ብሎ ማሰብ ያማል።” ብላለች።
ማእከሉ ለተገለሉ ወጣቶች ደህንነት የሚሰጥ ቦታ ሆኖ ያገለግላል። የጸሎት ቦታ ከመሆኑም በዘለለ ለማህበረሰቡ የቤተሰብ የምሽት ዝግጅቶች፣ የመጫወቻ ቤቶችን ለማዘጋጀት፣ የቅርጫት ኳስ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት እና ሌሎችም አገልግሎቶች ይሰጣል። በተጨማሪም የቤት ውስጥ የቅርጫት ኳስ እና ጂም ለመገንባት ትልቅ እቅድ እንዳላችው አህላም ትናገራለች።
ማእከሉ ጤናማ የሆነ የሰላም እና የጸሎት ቦታን ቢወክልም አመጸኞች ችግር ከመፍጠር አልተቆጠቡም። በደረሰው ጥቃት በማህበረሰብ አባላት ውስጥ ጭንቀት መፍጠሩ አይቀሬ ቢሆንም በተረጋጋ መንፈስ የአንድነት ትግሉን እያበረታቱ ካሉት ኢማማቸው የህያ ጋር በመሆን ችግሩን ለመቋቋም ችለዋል።
የህያ “ልዩነቶችቻችንን ችላ በማለት መላው ህብረተሰቡ መልዕክቱን ለማስተላለፍ መቀላቀሉ ድንቅ ነበር። አንድ ላይ ጠንካሮች ነን። አንድ ሰው ላይ የሚደርስ የጥላቻ ድርጊት ሁሉም የህብረተሰብ አካል ላይ እንደደረሰ ነው የምንቆጥረው።” ብሏል።