በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን እሁድ የሚውለውን ትንሳኤ በማሰብ ወደ እስራኤል ይጎርፋሉ። ይሁን እንጂ እስራኤል በ እርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ሁለት አመት የሞላት እና ህልውናዋን ጠብቆ ለማቆየት ከከበዳት ኢትዮጲያ ለሚመጡ መንፈሳዊ ተጓዦች የሚሰጠውን የጉዞ ፍቃድ ዳግመኛ እንድታጤንበት ተገዳለች።
በዚህ አመት በፌደራል መንግሥት እና በ ተቃዋሚው ህወሓት መሀከል የተኩስ አቁም ለማድረግ እየተደረገ ያለው ውይይት ጦርነቱ ወደ መቆም የሚሄድበት እድል እንዳለ የሚያሳይ ቢሆንም ባሳለፍነው አመት ጦርነቱ መቋጫ የሌለው ይመስልበት በነበረብት ግዜ ወደ እስራኤል የተጓዙ መንፈሳዊ ተጓዦች ከሚጠበቅባቸው ግዜ በላይ በእስራኤል መቆየት እና የከፊሎቹ ዛሬ ድረስ ወደ ሀገራቸው አለመመለስ ለክልከላው አንድ ሰበብ ነው።
የእስራኤል የህዝብ እና ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ለ አስጎብኚ ድርጅቶች በላኩት መግለጫ በኢትዮጵያ ባለው አለመረጋጋት ሳብያ “ተጓዦች ወደሀገራቸው አይመለሱም።” ብለዋል።
እስራኤል የጣለችውን እገዳ ተከትሎ የእስራኤል የውጪ አስጎብኚዎች ማኅበር ኃላፊ ዮሲ ፋታል ለሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አይለት ሻክድ በጻፉት ደብዳቤ ውሳኔው “እጅግ አድሎአዊ” ነው ሲሉ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የ የእስራኤል ባለስልጣናት እገዳው የተጣለው በኢትዮጲያ ባለው አለመረጋጋት ለመንፈሳዊ ጉዞው የሚመጡ ተጓዦች ወደ ሀገራቸው አይመለሱም ከሚል ፍራቻ መሆን ተናግረዋል።
ዮሲ በኢትዮጵያውያን ላይ የተደረገው ክልከላ አድሏዊ ነው ማለቱን ተከትሎ መልስ የሰጡት የሰጡት የእስራኤል ባለ ስልጣናት “ባለፉት አመታት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የገቡ በርካታ ተጓዦ ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ በህገ ወጥ መንገድ እስራኤል ውስጥ ቀርትዋል።” ብለዋል።
ዮሲ ለሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር በፃፈው ደብዳቤ ከባለፈው ፋሲካ ጀምሮ በእስራኤል በህገ ወጥ መንገድ የቆዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉ የሚለው ክስ እውነት ቢኖረውም እገዳው ግን ሁሉም ምዕመናን ከአመታዊ የአምልኮ ስርአታቸው እንዲገደቡ የሚያደርግ ነው ሲል በግልፅ ጠቅሷል።
“የእስራኤል መንግሥት በእስራኤል ድንበሮች ውስጥ በሚገኙት በሶስቱ ሀይማኖቶች ቅዱሳን ስፍራዎች ላይ የሚከናወን ሀይማኖታዊ የአምልኮ ነፃነት ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ኃላፊነት አለበት።” ሲል ዮሲ ተናግሯል። አስከትሎም ይህን ኃላፊነት አለመወጣት “የእስራኤልን መንግሥት ለጸሎትና ለአምልኮት ብለው ወደ ቅድስቷ ሀገር የሚመጡ ክርስትያን ኢትዮጵያዊያን ቱሪስቶች ላይ የእስራኤልን በሮች መዝጋት ማለት ነው።” ሲል ገልፆታል።
ምን አልባትም የዮሲ አቤቱታ ወይም ኢትዮጲያውያን ያስነሱት ጥያቄ ከሰሞኑ የእስራኤል ኤምባሲ፣ የእስራኤል ህዝብና ኢሚግሬሽን ባለስልጣን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በድጋሚ ተገናኝተው እገዳውን እንዲገመግሙት መንገድ ከፍቷል።
አካላቱ ባደረጉት ውይይት እገዳው ለሁለቱም ሀገሮች ጠቃሚ እንዳልሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሰውበታል። በእስራኤል የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደገለጸው ከእስራኤል ፓርላማ አባል ጋዲ ይባርከን ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያውያኑ እስከ ፋሲካ ድረስ ለጉዞ የሚዘጋጁበትን በቂ ጊዜ አስቀምጦ እገዳው መነሳቱን ገልጿል።