ኢልሃን በፖለቲካ በተቃዋሚዎቿ ተሃድሶ አራማጅ ስትባል በቀድሞ የአሜሪካ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ደግሞ ህገወጥ መሆኗ ይነገርላታል። በ2020 የትራምፕ ስልጣኑን በለቀቀበት አመት የ73 አመቱ ፍራንክ አንቶኒ ፑዙቶ በኮንግረሷ ኢልሃን ኦማር ላይ ማስፈራርያ አድርሷል።
ከ ኢልሃን በተጨማሪ ፑዙቶ ተወካይ ኤሪክ ስዋልዌልን እና ተወካይ አደም ሺፍን ላይ ዝቷል። ጥር 25/ 2020 ለ ስዋልዌል“ሰላም ሚስተር ስዋልዌል፣ ልገድልህ እየመጣሁ ነው!” የሚል መልእክት ልኮለት ነበር። ለሺፍ የላከው መልእክት “ሰላም ፣ እኔ የ MS-13 ሰራተኛ ነኝ። ዛሬ ማታ ለአዳም ሺፍ እየመጣን ነው። ጭንቅላቱን እንቆርጣለን።” ሲል የጽሁፍ መለክቱ ላይ ” MS-13 የተባለ አለም አቀፍ የወንጀል ቡድን ውስጥ መሆኑን ገልጿል።
የካቲት 3/2020 ላይ የተላከው የፑዙቶ ሦስተኛው መልእክት ለኢልሃን ነበር። ወደ ኢልሃን ቢሮ ደውሎ ስልኩን ላነሳው ሰው “ዛሬ እንደምገድላት ንገራት” ብሎ ስልኩን ዘጋው።
ኢልሃን በኢንስታግራም ላይ “በፖለቲካ ንግግሮች ውስጥ የጥቃት ንግግሮችን መጠቀም ለጥላቻ ማነሳሳት ነው በዚህም የተነሳ የኮንግረሱ አባላት የማያቋርጥ የግድያ ዛቻ የሚደርስባቸውን ሁኔታን እየፈጠረ ነው።ይበቃል!” በማለት ጽፋለች። እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2022 የፍሎሪዳ ወረዳ ዳኛ ዊልያም ኤፍ ጁንግ የ73 ዓመቱን ፍሎሪድያን የ15 ወር እስራት ፈረደበት።
ኢልሃን ተቃዋሚዎቿ ሲሳለቁባት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ባለፈው አመት መጨረሻ ህዳር 30 ላይ ኢልሃን ከተወካዮቹ ከራሺዳ ትላይብ፣ አንዴ ካርሰን እና ጀማል ቦውማን ጋር በመሆን በካፒቶል ሂል ንግግር አድርገዋል። እናም ዑመር በድምጽ መልእክት የደረሰባትን የግድያ ዛቻ በመክፈት ለጋዜጠኞቹ አሰምታለች።
ዛቻው ከመከሰቱ ከወራት በፊት ተወካይ ቦበርት ኢልሃን ላይ እያላገጠች ተሰብበው ለሚመለከቷት ሰዎች ስታወራ በቪዲዮ ተቀርጻለች። ቦበርት ከኢልሃን ጋር ስለነበረው የአሳንሰር ገጠመኝ ገልፆ “ከኋላ የተሸከመችው ቦርሳ የለም ስለዚህ ደህና ነን።” ስትል እያፈዘች ተናግራለች። ቦበርት “የጂሃድ ቡድን የሆነው ሰው ዛሬ ለመስራት ወስኖ መጥቷል። ብላ ኢልሃንን በአስህሙር ገልጻለች።
ቦበርት በመጨረሻ ለኢልሃን ደወለችላ እንዲሁም በትዊት ገጿ ላይ የይቅርታ መለክት እንዲህ ስትል ጽፋለች “ስለ ተወካይ ኢልሃን በሰጠሁት አስተያየት የተናደዱ የሙስሊሙ ማህበረሰቦችን ይቅርታ እጠይቃለሁ። አስከትላም “ከሷ ጋር(ከ ኢልሃን) በቀጥታ ለመነጋገር ወደ ቢሮዋ ሄጄ ነበር።”
ነገር ግን ቦበርት ለ ኢልሃን በቀጥታ መደወሏም ይሁን አንድምታው ከ ኢልሃን የታሪክ ስሪት ጋር በትክክል አይዛመድም። ኢልሃን: “በእርግጥም ከተወካይ ቦበርት ተደውሎልኝ ነበር ታድያ እኔን ሳንሱር ላይ ስለማግኘቷ በራሷ የፈጠረችውን ውሸት አስመልክቶ በቀጥታ ይቅርታ እንደምትጠይቀኝ ተስፋ አድርጌ ነበር። ነገር ግን ” ቦበርት ለእሷ እስላማዊ ጥላቻ አስተያየቶች እና የፈጠራ ውሸቶች ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ጎጂ እና አደገኛ አስተያየቶችን መስጠቷን በይፋ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነችም።”
ኢልሃን በዚህ አላበቃችም። “ይህ ታሪክ የተሰራ ነው። ትምክህተኝነት ስሜቷ በስራዋ የተሻለ እንደሚያደርጋት ማሰቧ ያሳዝናል።
ከዚህ የቦይበርት መሳለቂያ ጉዳይ በላይ ኢልሃን እና በሙስሊሞች ላይ የማያቋርጥ ኢላማ ያነገበ ጉዳይ ነው። ለዚያ ኢልሃን “ፀረ-ሙስሊም ጭፍን ጥላቻ አስቂኝ አይደለም እናም የሚለመድ መሆን የለበትም። ኮንግረስ በጥላቻ የተሞሉና እና አደገኛ የሙስሊም ታጋዮች የማይወገዙበት ቦታ ሊሆን አይችልም።