ከ አስር ሺህ በላይ ወንዞች ያላት እና የክረምቱ ወቅት ጠና ባለ ግዜ አየሩ በረዶ የሚሰራባት ከተማ የፀሀዩ ሀሩር ከሚለበልብበት የዐረብ ሀገራ ጋር የሚያመሳስላትን አንዳች አስገራሚ ነገር አግኝታለች። ዛሬ በሚኒያፖሊስ መንገዶች ላይ በዐረብ ሀገራት ጎዳና የተለመደው ሙስሊሞች ወደ ሰላት የሚጠሩበት የአዛን ጥሪ ቀን እና ላሊት መሰማት ጀምሯል።
ባለፈው ወር የሚኒያፖሊስ ከተማ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የከተማው ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ አዛን በድምፅ ማጉያ እንዲደረግ ፈቅደዋል። በተጨማሪም ከንቲባው “አዛን አብሮነትን እና ምቾትን ይለግሳል።” ብለዋል።
በዚህ አመት ለመጀመርያ ግዜ በረመዷን አዛን በድምፅ ማጉያ የተደረገ ሲሆን ይህ ግን የመጀመርያው በድምፅ ማጉያ የተደረገ የአዛን ጥሪ አይደለም። ከንቲባው ከሶስት አመት በፊት በረመዳን አዛን በድምፅ ማጉያ እንዲደረግ ፈቅደዋል።
ከንቲባው በሚኒአፖሊስ ሙስሊሞች በሚበዙበት የ ሴዳር ሪቨርሳይድ በሚገኘው የ ዳር አል ሂጅራህ መስጂድ አዛን በረመዷን ወር በ ድምፅ ማጉያ እንዲደረግ ፍቃድ ሰተዋል።
በቅርቡ የከተማው ካቢኔ አባል የሚሆነው ጀማል ኦስማን ለ ሆርን ማጋዚን እንደገለፀው ለመጀመርያ ግዜ በመንገድ ላይ አዛን የሰማበትን ቀን በግልፅ እንደሚያስታውሰው ይናገራል። “እጅግ ስሜታዊ ያደርግ ነበር።” ብሏል።
ከተማዋ በአማካይ ከ መቶ ሺህ የሚልቁ ሙስሊሞች ሲኖሩባት በየትኛውም የከተማው ጥግ ሙስሊሞች ይገኙባታል። ኦስማን የከተማውን ካቢኔ በ ቀጠና 6 አባል ሆኖ ለማገልገል በ ኦገስት 2020 ቃል ሲገባ አዛን በከተማዋ አመቱን ሙሉ እንዲፈቀድ እንደሚሰራ ቃል ገብቶ ነበር። ከሁለት አመት ባነሰ ግዜ ውስጥ የአዛን ጥሪ በከተማው ማስተጋባት ጀምሯል።
ኦስማን በ ከተማው አመቱን ሙሉ አዛን እንዲደረግ ከ ከተማው የከንቱባ አባልት እና ከከተማው ጠበቆች ጋር በጋራ ሰርቷል። ረቂቁን ካረቀቁ በኋላ ለካቢኔው ቀርቦ 13 የከተማው ካቢኔ አበላት በሚስጥር እንዲመርጡበት ተደርጓል።
ኦስማን አዛን ላይ ክልከላ እንዳልነበር ረቂቁም ይፋ እንዳደረገው ይገልፃል። ኦስማን “ረቂቁ አዛን በሚኒያፖሊስ ህጋዊ እንዲሆን ማድርጉን እናመሰግናለን።” ብሏል አስከትሎም “አዛን ለእምነታችን አስፈላጊ ከሆኑ ነግሮች መሀከል ወሳኙ ነው። በቀኑ ክፍለ ግዜ በከተመዋ እንዲሰማ ማድረጉ በከተማው ህግ ውስጥም ተካቷል።” ብሏል።
ኦስማን የቤተክርስትያን ደወል ህጋዊ ነው ልክ እንደዚሁም አዛን ህጋዊ ነው። ይሁን እንጂ ከጠዋቱ አንድ ሰአት በፊት እና ከምሽቱ አራት ሰአት በኋላ አዛን ማድረግ በከተማው ክልከላ መሰረት የተከለከል ነው። “ህግ ማክበር ላይ ግልፅ መሆናችን ሊታወቅ ይገባዋል።” ብሏል።
ሚኒያፖሊስ ዴርቦርን፣ ሚቺጋን እና ፓተርሰን ኒው ጀርሲን በመከተል አዛን የፈቀደች ሶስተኛዋ ከተማ ሆናለች። ይሁን እንጂ ምርጫው በ ፓተርስተን ከበድ ያለ ነበር 5 ለ 4 በሆነ ድምፅ የከተማዋን የድምፅ ብክለት ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ተንተርሶ የአዛን ፍቃድ ተፈዷል። የሚኒያፖሊስ ምርጫ ግን በሙሉ ድምፅ አዛንን ፈቅዷል።
በሚኒያፖሊስ ከሚገኝት የከተማዋ 13 የከተማው ምክር ቤት አባላት መሀከል በዛ ያሉት ከተለያየ አካባቢ የመጡ ናቸው። 7 አባላት ኮሎርድ ናቸው፣ ሰባት ሴቶች እና ሶስት ሙስሊሞችን ያቀፈ ነው። የተሰባጠረው የምክር ቤት አባል ከየትኛውም አካባቢ ለመጡ ሰዎች በራቸውን ክፍት ያደረጉ ናቸው። ይህም ይመስላል ምርጫው በማይታወቅበት መልኩ እንዲደረግ በር የከፈተው።