በሩሲያ እና ዩክሬን መሀል ያለው ግጭት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ጦርነቱን ለማምለጥ እየተሰደዱ ባሉ ዩክሬናዊያን ላይ ከፍተኛ ጫናን አሳድሯል። ስደተኞቹ በቁጥር ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሲሆን ይህም በሁለተኛው የአለም ጦርነት ሳብያ ከነበሩት ስደተኞች ቁጥር ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል።
አውሮፓውያኑ የዚህን መሰል ጦርነት ካዩ ከሰባ አምስት አመታት በላይ ቢያስቆጥሩም ከአውሮፓ ውጪ ላሉ ሀገራት ግን እንግዳ ነገር አይደለም። አንዳንድ ሃገራት አሁንም በጦርነት እየታመሱ ይገኛሉ። ይህንኑ የአለም የጤና ድርጅት ሃላፊ ዶክርተር ቴድሮስ አድሃኖም በሚያሳዝን መልኩ ገልጸውታል።
ዶክተር ቴድሮስ በ ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እየጠቆሙ “የትኛውም የአለም ክፍል ለሰዎች ጤንነት ይበልጥ አስጊ ሆኗል።” ሲሉ ተናግረዋል። አስከትለውም “ አሁን እያወራን ባለንበት ሰአት በረሃብ ምክንያት ሰዎች ህይወታቸውን እያጡ ነው።” ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ህልፈት፣ ለበርካቶች መፈናቀል እንዲሁም ባዶ መቅረት ምክንያት የሆነው አሰቃቂ ጦርነት ላይ ሆና አሁን ሁለተኛ አመቷን ይዛለች። ዶክተር ቴድሮስም አድሃኖም የህዝቡ ቅሬታ እና የሰባዊ እርዳታ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ላይና በዩክሬን በካከል ያሉ ልዩነቶችን ጠቁመዋል። አለም ለጥቁር ቀለም ህዝቦች እና ለነጮቹ ህይወት እኩል የሆነ ዋጋ ይሰጥ እንደሆነም ጥያቄ አንስተዋል።
እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን ላይ አሜሪካ ከዩክሬን የሚመጡ ስደተኞችን ለሚቀበሉ የአውሮፓ ሀገራት 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብታለች። በተጨማሪም በገንዘብ ማሰባሰቢያ ኮንፈረንስ ላይ በርካታ ሀገራት በዩክሬን እና በአጎራባች ሀገራት ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ ተግባር በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሌላ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አሰባስበዋል። ከኮንፈረንሱ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ይህ የሰብአዊ እርዳታ ጥሪ እስካሁን ካገኘናቸው በጣም ፈጣን እና ለጋሽነት ከተሞላበት ምላሾች ውስጥ አንዱ ነው” ብለዋል።
ከገቢ ማሰባሰቢያ ኮንፈረንሱ አንድ ሳምንት በፊት መጋቢት 25 ቀን ላይ ከስዊድን እና ስዊዘርላንድ ጋር በመተባበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን ያለውን ሰብአዊ ቀውስ አስመልክቶ ጉባኤ አድርጓል። በዓለማችን ትልቁን የሰብአዊ ቀውስ እያስተናገደች ላለችው ሀገር የመን ከሚያስፈልጋት 4.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አንድ ሶስተኛውን እንኳን መሙላት ያልቻለ ገንዘብ ተሰብስቧል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊነት ክፍል ዋና ሃላፊ ማርቲን ግሪፊዝ ከየመን ቃል ኪዳን ፕሮግራም በኋላ መከፋቱን ገልጿል። የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ኃላፊ ጃን እገላንድ በተሰበሰበው ገንዘብ ደስተኛ አለመሆኑን በግልጽ “የየመን ህዝብ ለዩክሬን ህዝብ ያየነው አይነት ድጋፍ እና ትብብር ያስፈልገዋል” ሲል ተናግሯል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ በሀገራቸው ያለውን ሰብአዊ ቀውስ በማውራት ብቻ አልተቆጠቡም። የመን እና ሶሪያን የመሳሰሉ ብዙ የተሰቃዩ እና አሁንም እየተሰቃዩ ያሉ ሀገራትንም ማንሳት ችለዋል። ዶክተር ቴድሮስ “አለም የሰውን ዘር እኩል እየተመለከተ እዳልሆነ ግልጽ እና ታማኝ ሆኜ መናገር አለብኝ። አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የበለጡ ናቸው።” ብለዋል።
በዩክሬን ውስጥ ላለው ቀውስ የተሰጠው ምላሽ ለሌሎች ሀገራት ቀውሶች ከተሰጠው ምላሽ የተለየ ሊሆን ቢችልም፣ የ “አሊያንስ ፎሪምፖወሪንግ ፓርትነርሺፕ አስተባባሪ የሆኑት” ስምሩቲ ፓቴል ክስተቱን ዘረኝነት አይደለም ብለዋል። “አንድ ነገር ቅርብ ሲሆን እና በቅርብ የሚታይ እንዲሁም ስሜቱ የሚሰማ ሲሆን ከሌሎች በጣም ርቀው ከሚገኙ ቦታዎች በተለየ ልብ የመንካት አቅም አለው።” ብለዋል። ስለዚህ “ከዩክሬን ጋር ያለው የእርዳታ ገንዘብ አለመመጣጠን ከዘረኝነት የመነጨ አይደለም” ሲል አክሏል።
ነገር ግን እንደ በ “ሴቭ ዘ ችልድረን” ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆነችው ጋብሪኤላ ዋኢማን ሌሎችም ነገሩን በግልጽ የተቃወሙ በርካቶች ናቸው። ጋብሪኤላ “በዩክሬን ያሉ ሕጻናት ያሳለፉት ነገር አሰቃቂና የኛን እርዳታ የሚጠብቅ ነው። ነገር ግን በተመሳሳይ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ እና ከቦምብ ድብደባ እና መፈናቀል የተረፉ እንዲሁም ካለ ምንም የቀሩ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉ ሌሎች ህጻናት አሉ። ለነሱም የኛ ፍቅርና አብሮነት ያስፈልጋቸዋል።” ብላለች።
ፓቴል ርቀው በሚገኙ ቦታዎች ባሉ ህጻናት ላይ ትኩረት እያረገ ቢሆንም ከዩክሬን ለራቁ ሀገራት ሃዘኔታ ሲጎርፍ እንዳየነው ሁሉ ዛሬ እየኖርንበት ያለው አለም አቀፍ ማህበረሰብ እነዝያን ልጆች ሃዘናቸውን ተጋርቶ ይበልጥ ቅርብ ያደርጋቸዋል።