ኮቪድ በብዙ ባልተጠበቁ መንገዶች ተጽእኖ አድርጎብናል። በስራ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በትምህርት ህይወታችን በርከት ያሉ ለውጦችን አስተናግደናል። ኮቪድን ተከትሎ የህወታችን አካል የሆኑ አንዳንድ አዳዲስ ክስተቶች አሁንም ከኛው ጋር የሚቆዩ እንጂ በቅርብ ግዜ ከህይወታችን የሚወጡ አይመስሉም።
ብዙ ድርጅቶች አሁን ሠራተኞቻቸው በቋሚነት ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ፈቅደዋል። ነገር ግን ትምህርት ቤት በመላው አገሪቱ ከተጋረጠው የኮቪድ ተፅእኖ ለማምለጥ የተለየ ስራ ይፈልጋል።
እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2020 መላው ሀገሪቱ መተግበሩ ግድ ከሆነው የርቀት ትምህርት በተጨማሪ በ 2020-2021 እና 2021-2022 የትምህርት ዓመታት ውስጥ ብዙ ትምህርት ቤቶች በሳምንት ለ 4ቀናት ትምህርት መስጠት ጀምረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ነው። አርብን ትምህርት የለለበት ቀን ማድረግ በቀላሉ ሊተው የሚችል አልሆነም።
በተጨማሪም በመጋቢት ወር በደቡብ ምስራቅ ቴክሳስ ውስጥ የሚገኘው ሁል ዴዪስታ ኢንዲፔንደንት ስኩል ዲስትሪክት ለ 2022-2023 የትምህርት ዘመን አራት ቀናት ትምህርትን ለመከተል ወስኗል። በቴክሳስ የሚገኘው ሚኒራል ዌልስ በ2022-2023 የትምህርት ዘመን ወደ የአራት-ቀን የትምህርት ሳምንት ለመሸጋገር ወስኗል። ሚነራል ዌልስ በ2021-2022 የትምህርት አመት መጨረሻ ላይ በተወሰኑ መሰናክሎች መመታቱ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጦችን እንዲያደርግ አስገድዶታል።
ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ሚነራል ዌልስ ከአስተማሪዎቹ መሀከል ተወዳጅ የተባለውን መምህር አጥቷል። ከዚያ በኋላ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በአስር ቀናት ጊዜ ውስጥ ስድስት ተጨማሪ መምህራንን አጥቷል። አስተዳዳሪዎችም ከጊዜ በኋላ መምህራኑ አቋርጠው በሳምንት ለአራት ቀናት ትምህርት ወደሚሰጡ ሌሎች ወረዳዎች ለመስራት እንደሚመርጡ ተገንዝበዋል።
“የምንከፍለው ምንም ይሁን ምን መምህራንን በዚያ የአራት ቀን የትምህርት ሳምንት ማጣት ጀመርን” ሲል የሚነራል ዌልስ ረዳት የበላይ ተቆጣጣሪ ዴቪድ ታርቨር ተናግሯል። “ይህ ትልቅ የዓይን ከፋች ነበር።”
ሚነራል ዌልስ መምህራንን በሌሎች ትምህርት ቤቶች ካጣ በኋላ ብዙም ምርጫ አልነበረውም። ወረዳው ወደ 3,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን የሚያገለግል ሲሆን ተጨማሪ መምህራን የማጣት አቅም አልነበረውም።
ታርቨር “የተለያዩ አገልግሎቶችት የሚሰጡ አስተማሪዎች ነበሩን” ብሏል። “መምህራንን መቅጠር ላይ የተወሰነ ጥቅም አግኝተናል።” ብሏል።
የመምህራን ስራ መልቀቅ ቴክሳስ ላይ ብቻ የተከሰተ ሳይሆን መላው ሀገሪቱ እያጋጠማት ያለ ክስተት ነው።
ኔቫዳ በአሁኑ ጊዜ 3,000 ያልተሞሉ የመምህራን ክፍት የስራ ቦታዎች አሏት። በ2021-2022 የትምህርት ዘመን ኢሊኖይ በ88% ስቴት ዲስትሪክቶች 2,040 የመምህራን የስራ መደቦች ያልተሞሉ ወይም ብቃት በሌላቸው ሰራተኞች የተሞሉ እንደሆኑ ታውቋል።
ሚኒሶታም ከመምህራን እጥረት ካጋጠሙት ሀገራት አንዱ ነው። የሚኒሶታ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ዴብ ሄንተን “ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል እጥረት አለ።” ብለዋል። “የምትሰሙት እውነት ነው። ብዙ ወረዳዎች አሁንም የስራ ቦታዎችን ለመሙላት እየሰሩ ነው።
ሚኒሶታ የመጀመሪያ ዲግሪ እስካላቸው ድረስ የማስተማር ፈቃድ ሳይኖራቸው መምህራንን መቅጠርን ፈቅዷል። ልምድ ለሌላቸው አስተማሪዎች በኤስ ፓዉል ውስጥ ያሉ የትምህርት ቤት ሥርዓቶች የማማከር አገልግሎት እና በሥራ ላይ ሥልጠና ይሰጣሉ። ካለፈው መስከረም ጀምሮ የአኖካ-ሄኔፒን ትምህርት ቤት ዲስትሪክት 175 ክፍት የስራ መደቦች ነበረው። ምናልባትም እንደ ሚኒሶታ፣ ኔቫዳ እና ኢሊኖይ ያሉ ቦታዎች ከቴክሳስ እና ፍሎሪዳ የአራት ቀን የትምህርት ሳምንት ማበረታቻ ልምድ ሊወስዱ ይችላሉ።
የአሜሪካ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዳን ዶሜኔክ “የዚህን ያህል ከባድ ሆኖ አይቼው አላውቅም” ብለዋል። “በአሁኑ ጊዜ ትምህርት ቤቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮች አንደኛ ደረጃን ይዘዋል።”
በቴክሳስ ውስጥ ያሉ ወረዳዎች እና ሌሎች አራት ቀናትን ሲጠቀሙ የወላጆች ጥያቄ የአራት ቀናት ውጤታማነት ከእድሞው አምስት ቀናት ጋር በማነጻጽር ነው። በፍሎሪዳ የሚገኘውን የፖልክ ትምህርት ቤት ዲስትሪክትን በተመለከተ የአራት ቀናት የትምህርት ጊዜን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሁለት ዓመት አለው። በዚያ ወረዳ ውስጥ ያለው የትምህርት ሳምንት በ2022-2023 እና በ2023-2024 የትምህርት ዓመታት ውስጥ አራት ቀናት እንደሚሆን ይፋ አድርጓል።
በአራት ቀናት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በተማሪዎች የአካዳሚክ ስኬት ላይ የተደረጉ ጥናቶች ሰፋ ያሉ ግኝቶችን አውጥተዋል። ለምሳሌ፣ በኮሎራዶ ውስጥ የአራት ቀን ትምህርት ቤቶችን የተከታተሉ ተማሪዎች በኦርጋን ካሉ ተማሪዎች በሂሳብ እና በቋንቋ የላቀ ውጤት አግኝተዋል። በሌሎች ሁኔታዎች የታየው ግኝት ተቃራኒ ነበር።
የአራት ቀን የትምህርት ሳምንት የአምስት ቀን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ጊዜ መልሱን ይሰጠናል። ነገር ግን እስከዚያው ድረስ አርብ ጥዋት ላይ መተኛት ስለሚያጣትሙ በአንዳንድ ወረዳዎች የመምህራን እጥረት ሊቀንስ ይችላል።