በወርቅ እና ብር የምንገበያይበት ግዜ አልፏል። በእጃችን ያለው ጥሬ ገንዘብም ቢሆን በዛ ያሉ ተግዳሮቶች ስላሉበት ብድር ፈጣን እና ወሳኝ አማራጭ ሆኖ መቷል። ለትምህርት ክፍያ፣ ለቤት ወይንም ለንግድ በጥሬ ገንዘብ መተማመን አያዋጣም። ይሁን እንጂ ጠቀም ያለ ብድር ሀብት ለመገንባት ወሳኝ የሆነውን መዋዕለ ንዋይ የምናገኝበት አማራጭ ሆኗል።
የትኛውም አበዳሪ ብድር ለመስጠት ተበዳሪው ብድሩን ለመክፈል ብቁ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ይፈልጋል። ለዚህ ነው ለቤት፣ ለመኪና ወይንም ለንግድ አስፈላጊውን ብድር ለማግኘት ከዚህ በፊት የነበረ የብድር ታሪክ የሚታየው።
መክፈል የማይችሉትን ብድር መውሰድ የማይወጡት አዙሪት ውስጥ ይከታል። የተበደሩትን ለመክፈል ሌላ ብድር እሱን ለመክፈል ደግሞ ሶስተኛ ዙር እንድንበደር እያስገደደን ማለቅያ የሌለው አዙሪት ውስጥ ይከተናል። ይሁን እንጂ ለቀጣይ ህይወታችን እንዲጠቅመን ለትምህርት ወይንም ለ ንግድ ስራ አቅደን ብንበደር ጥቅሙ ላቅ ያለ ነው።
የብድር ደረጃችንን ለማሳደግ የብድር ካርድ መጠቀም ቀላሉ አማራጭ ነው። በተደጋጋሚ በተጠቀምነው ቁጥር የብድር ደረጃችንም ከፍ ይላል። ወጪያችንን ከመቆጣጠር በዘለለ የብድር ካርዳችንን በመጠቀም የአየር መንገድ ቅናሽ ወይ በገዛነው ልክ ተጨማሪ ጉርሻ ማግኘትን ጨምሮ የብድር መጠናችንን መጨመር ስንችል ከቆጠብነው ገንዘብ ላይ ቀጥታ ተቀናሽ የሚሆነውን የዴቢት ካርድ መጠቀም ጥቅሙ እምብዛም ነው። የብድር ካርድን መጠቀም ወለዱ ብዙ ነው ብሎ መስጋትም አስፈላጊ አይደለም! አጠቃላይ ብድሩን በየወሩ ከከፈልን ያለምንም ተጨማሪ ወለድ ብድራችንን መክፈል እንችላለን።
የብድር ደረጃዎን ሲያሻሽሉ የተሻሉ ሽልማቶችን የያዙ የብድር ካርዶችን ይሰጡዎታል። ለምሳሌ የአሜሪካን ኤክስፕረስ ሂሳብ በከፈቱ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ 3,000 ዶላር እስካወጡ ድረስ እስከ 50,000 ዴልታ ስካይ ማይልስ ይሰጣል። ለዚህ ነው በባንክ ካለን ሂሳብ ቀጥታ ተቀናሽ የሚያደርገውን ዴቢት ካርድ ከመጠቀም ይልቅ በብድር ካርድ በሶስት ወራት ለ ቤት ውስጥ ወጪዎች እና ለሌሎች አስፈላጊ ክፍያዎች 3 ሺህ ዶላር መጠቀም የሚመከረው። ከዚህ የሚገኘው 50,000 ዴልታ ማይልስ እንደ ግዜው ሁኔታ በአሜሪካ ውስጥ የደርሶ መልስ ትኬትዎን ይሸፍንልዎታል።
ብዙ ተጓዥ ካልሆኑ ደግሞ ካፒታል ዋንን ቢጠቀሙ ላወጡት እያንዳንዱ ዶላር የተወሰነ ገንዘብ ተመላሽ ይደረግልዎታል። አንዳንድ ማስታወቅያዎች 10,000 ዶላር አውጥተው ለተጠቀሙ ግለሰቦች 1,000 ዶላር ተመላሽ ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰው የዚህ ነፃ ገንዘብ ተቋዳሽ አይሆንም። ስለዚህ ጥሩ አቅርቦቶችን ለማግኘት የብድር ደረጃን ማሻሻል አስፈላጊ ነው።
ከዚህ ቀደም የብድር ካርድ ካልበነርዎ እና በተደጋጋሚ የብድር ካርድ ለማውጣት ጠይቀው ውድ ቢደረግብዎ አይጨነቁ። አንድ ጥናት እንዳሳየው 13% አሜሪካውያን የብድር ታሪክ የላቸውም ልክ እንደዚሁ 20% አሜሪካውያን ደግሞ እንዴት ብድር መገንባት መጀመር እንደሚችሉ እርግጠኛ አይደሉም። ለዚህ ደህንነቱ የተጠበቀ የብድር ካርድ መክፈት ጥሩ መፍትሄ ነው።
ደህንነቱ የተጠበቀ የብድር ካርድ እርስዎ ተቀማጭ በሚያደርጉት ጥሬ ገንዘብ ይደገፋል። ለምሳሌ በባንክ ሂሳብዎ ውስጥ 300 ዶላር ቢኖር በተመሳሳይ የገንዘብ መጠን የ300 ዶላር የብድር ካርድ ቢቀበሉ እና በወር ውስጥ ይህንን ገንዘብ ቢያጠፉት ብድሮን በባንኮ ካለው ገንዘብ ቀጥታ መክፈል ይችላሉ። ይህንን ለአንድ አመት በየወሩ ቢተገብሮት የብድር ደረጃዎ ከፍ ይላል። እነዚህ ደህንነታቸው የተጠበቁ የብድር ካርዶች በዌልስ ፋርጎ የአሜሪካ ባንክ እና በሌሎች ባንኮች ይሰጣሉ።
አንዴ ብድር ከገነቡ እና የብድር ደረጃዎን ለማሳደግ የብድር ካርድዎን መጠቀም ከጀመሩ በኋላ ለተወሰኑ ወራት በ 0% አመታዊ ወለድ ስሌት በሚሰጥዎ አማራጭ ይደነቃሉ። ለምሳሌ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ለ 12 ወራት ወይም ከ 15 እስከ 18 ወራት ያለምንም ወለድ ዝቅተኛውን የክፍያ መጠን ከ 50$ ያነሰ ክፍያ ብቻ እንዲከፍለ ያመቻችሎታል። እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ አሪፍ የብድር መጠን ላላቸው ደግሞ ግዜው ይጨምራል።
በእርግጥ የብድር ካርድ አበዳሪዎች በየወሩ ዝቅተኛውን ክፍያ እንዲከፍሉ የሚጠይቁት ወለድ ለመሰብሰብ ነው ይሁን እንጂ ይህ ወለድ በዚህ ግዜ የሚታሰብ አይደለም።