በዘንድሮው የአለም ዋንጫ አምስት ሀገራት አፍሪካን ወክለው ይጫወታሉ። ከሀገራቱ ዝርዝር ውስጥ የመጀመርያውን ደረጃ የያዘው የሴኔጋል ቡድን ይህን ጨዋታ ሲያደርግ ለሁለት ተከታታይ ጊዜ ይሆናል። ሴኔጋል በአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች የተባለውውን ሳዲዮ ማኔን ይዞ የአለም ዋንጫን በአሸናፊነት የማጠናቀቅ እድል ይኖረዋል?
እ.ኤ.አ. በ 1930 የዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ወዲህ አንድም የአፍሪካ ቡድን ዋንጫ አልወሰደም።ነገር ግን አንድ ቡድን አፍሪካ እስካሁን ካየቻቸው ተጫዋቾች ምርጥ የተባለውን ተጫዋች እንደያዘ መናገር ከጀመረ ሰነባብቷል። የሰላሳ አመቱ ማኔ በ2021 ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫን እንድታሸንፍ አድርጓታል።ነገር ግን ከዛ ቀደም ብሎም ማኔ በርካታ ሪከርዶችን ሲሰብር ነበር።
እ.ኤ.አ. በ2015 ማኔ አስቶንቪላ ላይ ከሶስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሶስት ጎሎችን በማስቆጥር የመጀመሪያው ነው።ሶስት ጎሎችን በማስቆጠሩ አሁንም በታሪክ ፈጣኑ የፕሪምየር ሊግ ሀትሪክ ሪከርድን እንደያዘ ነው።
በ2018 እና 2019 በዩኤኤፍ ሻምፒዮንሺፕ የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ሊቨርፑልን በተከታታይ ጨዋታ መርቷል።ሊቨርፑል በ2018 ከሪያል ማድሪድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ቢሸነፍም በ2019 ቶተንሃም ሆትስፐርን አሸንፏል።በተመሳሳይ አመት ማኔ ፒየር-ኤመሪክ ኦባሚያንግ እና ሞሃመድ ሳላህን በ 2019 በፕሪምየር ሊጉ ብዙ ግቦችን በማስቆጠር አቻቸው ሆኗል።
ማኔ በዝያ አላቆመም። በተለያዩ ምክኛቶች ተራዝሞ እ.ኤ.አ. በጥር-የካቲት 2022 በተደረገው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማኔ የሴኔጋልን ብሄራዊ ቡድንን በመምራት የፍጻሜ ጫዋታውን ከግብፅ ጋር አድርጓል። በሻምፒዮና ጨዋታው ሌላኛውን የአፍሪካን ድንቅ ተጫዋች በመሀመድ ሳላህን ገጥሟል።
ሴኔጋል በሩብ ፍፃሜው ኢኳቶሪያል ጊኒን 3-1 ካሸነፈ በኋላ በግማሽ ፍጻሜው ቡርኪናፋሶን 3-1 አሸንፏል። በፍፃሜ ጨዋታውም ሴነጋል አሸንፎ የማያውቀውን የአፍሪካ ዋንጫ ለሰባት ግዜያት በማሸነፍ ዋንጫ ከወሰደው ከግብፅ ጋር ተገናኘ። ግን ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ትንሽ ለየት ያለ ነበር። በፍጻሜ ጫዋታው ውድድሩ የማኔ እና የ ሳላህ ነበር። ሆኖም ማኔ የውድድሩን ፍጻሜ መወሰን ችሏል።
በጨዋታው ሰአት 0-0 ተጠናቀቀ። ተጨማሪ ሰአት ተሰጥቶ በተደረገው የፍፁም ቅጣት ምቱ ማኔ ሴነጋልን ለድል ያበቃችዋን የቅጣት ምት አስቆጥሮ ሴንጋጋል ግብጽን 4-2 እንዲያሸንፍ አስችሏል። ማኔ በድምሩ 3 ጎሎችን እና ሁለት የተመቻቹ ኳሶችን በማቀበል ‘የአመቱ ድንቅ የአፍሪካ ዋንጫ ተጨዋች’ ተብሎ ተመርጧል። ይህም ለእሱ እና ለሴኔጋል በኳታር ለሚደረገው የአለም ዋንጫ ዝግጅት የሚያስፈልጋቸውን አቅም ሰጥቷቸዋል።
ማኔ ግብፅን ካሸነፈ በኋላ “የቻምፒዮንስ ሊግ እና አንዳንድ ሌሎች ዋንጫዎችን አሸንፌያለሁ ነገርግን ይህ ለእኔ ልዩ ነው” ብሏል። “ይህ ለእኔ የበለጠ አስፈላጊ ነው።” ሲልም አክሏል።
ከአፍሪካ ዋንጫ ድል በተጨማሪ ባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ ሴኔጋል እና ግብፅ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ግጥምያ አድርገዋል። እንደቀድሞው ሁሉ በጫወታው 1 1 አቻ በመሆናቸው በድጋሚ በመለያ ምት ሴንጋል ግብጽን 3-1 አሸንፏል።
ታድያ በዚህ ብቃት ወደ ኳታር ሲሄዱ ሴኔጋል ብቻ አይደለም ለራሱ ከፍ ያለ ግምት የሰጠው። እ.ኤ.አ. በ1998 ፈረንሳይ በአለም ዋንጫ ስታሸንፍ ለፈረንሣይ የተጫወተው ፍራንክ ሌቦውፍ “ሴኔጋል ለእኔ ከዓለም ዋንጫ ተወዳጅ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ነው።” ብሏል። “በእርግጥም የአለም ዋንጫን ማሸነፍ የሚችሉ ይመስለኛል።”
የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ስራ አስኪያጅ አሊዩ ሲሴ የሌቦኡፍን ሀሳብ አስተጋብቷል። ሲሴ “የአፍሪካ ዋንጫን ካሸነፍክ ቀጣይ ግጥሚያዎችን እንዴት መጫወት እንዳለብህ ማወቅ አለብህ” ብሏል። “በኳታርም ቢሆን የተሻልን እንሆናለን። በ2018ቱ የአለም ዋንጫ በቡድን ደረጃ ላይ ሆነን ከጫወታው ለመሰናበት ተገደናል። ዛሬ ግን አድገናል።” ብሏል።
ሴኔጋል በአፍሪካ ውስጥ ምርጡ ቡድን በመሆኑ በዚህ አመት ዘውዱን ለመውሰድ ካለፉት አመታት የተሻለ እድል ቢኖረውም ከሴኔጋል የተሻሉ ብዙ ቡድኖች በውድድሩ ዝርዝር ውስጥ አሉ። እ.ኤ.አ. በ2021 ፊፋ ሴኔጋልን ከአለም 20ኛው ምርጥ ቡድን አድርጎ አስቀምጧል። በ2022 ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል ወደ 18ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ከሴኔጋል በተጨማሪ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ካሜሩን እና ጋና አፍሪካን ወክለው በአለም ዋንጫ የሚጫወቱ ይሆናል። ጋና በአለም ዋንጫ ስትሳተፍ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።
ለማኔ እና ለሴኔጋል አሸናፊነትን ለመጎናጸፍ ይህ የመጨረሻ እድላቸው ይሆናል? የማኔ ፍጥነት እና የማጣጠፍ ችሎታው በጣም አስደናቂ ነው። ነገር ግን በሠላሳ ዓመት ዕድሜው ምናልባትም ይህ ለሱ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ሊሆን ይችላል።በ 2026 በአሜሪካ ውስጥ በሚዘጋጀው ቀጣዩ የአለም ዋንጫ ማኔ በሠላሳ አራት አመቱ መጫወት ላይችል ይችላል።
ምንም እንኳን ሴኔጋል በ 2002 የአለም ዋንጫ ላይ ግማሽ ፍጻሜ ላይ በመድረስ በውድድሩ ረጅም ቆይታ ቢኖራትም ይህ አመት ግን ለሴኔጋል ምርጡ አመት የሆነ ይመስላል። በዚኛው ውድድር ዝነኛውን ቡድን አሸናፊ የማድረግ ዋናው ሃላፊነት ያለበት ማኔ ነው።