የ ስኳር ህመምተኞች የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲኖርባቸው ከዚሁ ጎን ለጎን ስኳርን የሚተኩ አማራጮች ጥቅም አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ማወቅ አለባቸው። ሰው ሰራሽ ጣፋጮች የስኳር ህመምተኞች የ A1-C ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የሚረዱ ቢሆንም አንዳንድ አማራጮች በተጓዳኝ የ ኮሌስትሮል መጨመር፣ የካንሰር አደጋዎች እና ሌሎች የጤና እክሎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ስለዚህ የሰው ሰራሽ ጣፋጮች ጥቅሞች እና ጉዳቶች ምንድናቸው? የሚለውን መመለስ አለብን። በአሜሪካ የምግብ እና የመድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተፈቀዱ አነስተኛ ካሎሪ ያላቸው ሰው ሰራሽ ጣፋጮች በዚህ መልኩ ቀርበዋል፦
ጥቅሞች
ስቴቪያ ከካሎሪ ነፃ የሆነ ጣፋጭ ሲሆን የተሠራው ስቴቪያ ሪባውዲያና ከተሰኘ መልካም መዓዛ ካለው ተክል ነው። ከእውነተኛው ስኳር 300 እጥፍ ጣፋጭነት ያለው ሲሆን እንደ ምግብ ደህንነት እና ቁጥጥር ባለስልጣን ከሆነ አንድ ግለሰብ ባለው የሰውነት ክብደት ልክ በ አንድ ኪሎግራም 4 ሚሊግራም ስቲቪያ መጠቀም ይችላል። የ ዲያቢተስ 2 ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦችን ይረዳል ተብሎ የታመነው ደግሞ ታጋቶስ ነው። ይህ ጣፋጭ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረትን ለመዋጋት ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር በዝቅተኛ የ ግላይሴምክ ኢንዴክስ አመጋገብ ላይ ያሉ የስኳር ህመምተኞችን ይረዳቸዋል፡፡
አብዝሀኛው ሰው ሰራሽ ጣፋጮች በሙቀት ወቅት ጥፍጥና እና ቃናቸውን የሚቀይሩ ሲሆን ሱክራሎስ እና ኒኦታሜ ግን በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ጭምር ጥፍጥናቸውን ስለማይቀይሩ ጣፋጭ ለመጋገር ጠቃሚ ናቸው። በቀን ውስጥ አምስት ሚሊግራም ሱክራሎስ ለአንድ ኪሎግራም የሰውነታችን ክብደት መውሰድ ጠቃሚ ሲሆን ከተለመደው ስኳር 600 እጥፍ ጥፍጥና አለው።
እንደ አስፓርታም ሁሉ ከተለመደው የስኳር ጥፍጥና 200 እጥፍ የሚጣፍጠው አሲልፋም ፖታሺየም ደህንነቱ የተረጋገጠ ነው። በቀን 15 ሚሊግራም ለ አንድ ኪሎግራም የሰውነታችን ክብደት መውሰድ ይመከራል። ሳካሪን በበኩሉ ዝቅተኛ ካሎሪ የያዘ ጣፋጭ ነው። ከ ስኳር ከ 200 እስከ 700 እጥፍ ጣፋጭ ሲሆን በየቀኑ 15 ሚሊግራም ሳካሪን ለ አንድ ኪሎግራም የሰውነታችን ክብደት መውሰድ ያስፈጋል።
ጉዳቶች
አስፓርታም አንዳንድ የአሚኖ አሲድ፣ የአስፓርቲክ አሲድ፣ የፊኒላላኒን እና አነስተኛ ኤታኖል የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።
እንደ ህመም ማስታገሻ እና በሰውነት ላይ የሚፈጠር መጉረብረብን ለመቀነስ ያለው ጥቅም ጎላ ያለ ቢሆንም በጤና ላይ የሚያስከትለው ተጓዳኝ ጉዳት አወዛጋቢ አድርጎታል። ይህን ጣፋጭ ከወሰዱ በኋላ በአንዳንድ ትብ ግለሰቦች ላይ እንደ እብጠት ያሉ የአለርጂ ምልክቶች ተስተውለዋል።
ይሁን እንጂ ከዚህም ባሻገር ይህ ጣፋጭ ሌሎች የጎንዮሽ የጤና እክል በማስከተሉ አነጋጋሪ ሆኗል። በጣፋጩ ላይ የተደረገ ጥናት እንዳሳየው ቶሎ ምላሽ የሚሰጡ ትብ ግለሰቦች ላይ እብጠት እና የአለርጂ ምልክቶች ታይቷል። ነገር ግን ለእዚህ አለርጂ መፈጠር ሰበብ የሆነው የአስፓርተም ንጥረ ነገር የትኛው እንደሆነ አልታወቀም።
ሳካሪን በ 1879 በሬምሰን እና በፋህልበርግ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ጣፋጭ ነው። ሆኖም ስኳርን የሚተኩ ሰው ሰራሽ ጣፋጮች ላይ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ይህ ጣፋጭ የሰውነት ክብደት መጨመር ያስከትላል። በቤተ ሙከራ አይጦች ላይ የተሰራ ሌላ ጥናት ይህ የሳካሪን ጣፋጭ የፊኛ ካንሰር የሚያስከትል መሆኑ በመታወቁ በ 1977 በ አሜሪካ እና ካናዳ ገበያዎች ላይ እንዳይሸጥ ታግዶ የነበረ ሲሆን በሰዎች ላይ ተመሳሳይ ጉዳት ያስከትላል? የሚለውን የሚመልስ በቂ መረጃ ባለመገኘቱ በድጋሜ ወደ ገበያ ተመልሷል።
የካንሰር አደጋ
የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሱራክሎስ ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ቢሰጥም በቤተ ሙከራ አይጥ ላይ በተደረገ ጥናት አደገኛ የሆነ እጢ እንዲፈጠር ሰበብ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ እጢ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚያዛመት አደገኛ ካንሰር ነው።
በ 1970ዎቹ መጀመሪያ በቤተ ሙከራ አይጦች ላይ በተደረገ ጥናት ሳካሪን ለ ሽንት ፊኛ ካንሰር መፈጠር ሰበብ መሆኑ ተጠቁሞ ነበር። ይሁን እንጂ ጥናቱ ይህን የሚያስከትለው በአይጦች ላይ ብቻ መሆኑን አሳይቷል። እስካሁን በሰው ልጆች ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ የሚያሳይ መረጃ ባለመኖሩ ለስኳር አማራጭ መተክያ ሆኖ እንዲቀርብ ተፈቅዷል። ይሁን እንጂ ተጠቃሚዎች ይህንን አማራጭ ከመጠቀም እኩል የሚሰሩ አዳዲስ ጥናቶችን መከታተል አለባቸው።
የክብደት መጨመር
ለክብደት መጨመር እንደ ምክንያትነት በተደጋጋሚ የሚነሳው ጣፋጭ አሲሱልፌም ፖታሺየም ነው። በአይጦች ላይ በቤተ ሙከራ በተሰራ ጥናት የክብደት መጨመር እንደሚያስከትል ተረጋግጧል። ጥናቱ እንዳሳየው ጣፋጩ ተጠቃሚዎቹ ላይ የሚስተዋለውን የአልሚ ምግብ እጥረት ከመቅረፍ ባሻገር ተጨማሪ ጣፋጭ ምግቦች የመመገብ ፍላጎት እንዲጨምር ያደርጋል። ነገሩን የሚያወሳስበው በላብራቶሪ አይጦች ላይ የተደረገው ጥናትም አይጦቹ በጣፋጭ ሱስ መያዛቸው መስተዋሉ ነው።
በላብራቶሪ አይጦች ላይ በተደረገው ሙከራ 36% የሚሆን ከፍተኛ ለሜታብቦሊክ ሲንድሮም ተጋላጭነትን ያሳየ ሲሆን ይህም ለልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። በተጨማሪም ለ ታይፕ 2 የስኳር ህመም ተጋላጭነት በ 67% ይጨምራል።
ምቾት የሚነሱ ስሜቶች
ምንም እንኳን ጣፋጮቹ አነስተኛ የካሎሪ መጠን ቢኖራቸውም ከተመገቡት በኋላ ምቾት የሚነሱ ስሜቶችን ሊያስከትል ይችላል። ስቲቪያን እንደ ምሳሌ ብንወስ ከተጠቀሙት በኋላ በ አንዳንድ ሰዎች ላይ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ የሆድ መነፋት እና የሆድ ህመም ይሰማቸዋል። ታጋቶሴ በበኩሉ የማቅለሽለሽ፣ የሆድ መነፋት እና ተቅማጥ ያስከትላል።
በስቴቪያ መራራ ጣዕም ምክንያት አንዳንድ ኩባንያዎች ምሬቱን ለመቀነስ ሲሉ አነስተኛ ስኳር ይጨምሩበታል። ነገር ግን ይህ ስኳር በስቴቪያ ውስጥ ያለውን የካሎሪ መጠን ከፍ በማድረግ ይሰጥ የነበረውን ጥቅም እንዲቀንስ አድርጎታል።
የተሻሉ አማራጮች
ፍራፍሬዎች ስኳርን ለመተካት ሌላ ተፈጥሯዊ አማራጭ ናቸው። ሙዝ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ጣፋጮችን በምግብ ውስጥ እና በመጠጥ መሀል በመቀላቀል ጣፋጭ ጣዕም እንዲኖራቸው ማድረግ እንችላለን።
ማር ከስኳር ያነሰ ካሎሪ እና እርጥበት ስላለው ከስኳር ይልቅ ማርን መጠቀም ለጤን ተመራጭ ነው። ማር ማዕድናትን፣ ቫይታሚኖችን እና ፀረ-ሙቀት አማቂዎችን ይይዛል። አንድ ምግብ በፀረ-ሙቀት-አማቂዎች የበለፀገ ከሆነ እንደ ልብ ህመም ያለ እና በተጨማሪ የካንሰር በሽታዎች የመያዝ እድልን ይቀንሳል። ይሁን እንጂ የስኳር ህመምተኞች ከተገቢው በላይ ማር በመጠቀም የሚፈጠርን በደም ውስጥ የሚገኝ ስኳር መጨመር ለመከላከል የሚወስዱትን የማር መጠን መመጠን ላይ መጠንቀቅ አለባቸው።