ለብዙ ዘመናት ለጡረታ ጊዜ ስለማቀድ ምንም አይነት ሀሳብ አልነበረም። እንዳሁኑ ህይወት ከመክበዱ በፊት ሰዎች በቀላሉ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቅርበት ይኖሩ ነበር። የነበረባቸው ወጪ አነስተኛ ስለነበር ወላጆች እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ልጆቻቸው ለመኖር ዋስትናቸው ነበሩ። ዛሬ ግን ዘመን ተለውጦ አንዳንድ አሜሪካዊያን የጡረታ እድሜያቸው ላይ ሲደርሱ ቤት አጥ ሆነው ወደ ጎዳና ለመውጣት ሲገደዱ እንዲሁም በህይወት ለመቆየት ግብ ግብ ሲፈጥሩ መመልከት ለጡረታ ጊዜ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አስተምሮናል። በፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በኒውዮርክ ከተማ ዕድሜያቸው 50 እና ከዚያ በላይ በሆኑ አረጋውያን የተያዙት ቤት አልባ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጡ መጠለያዎች “በ2017 ከ17,000 በላይ የጨመሩ ሲሆን ይህም ከ2004 በሦስት እጥፍ ገደማ ጨምሯል። እንዲሁም “ይህ አኃዝ በ2030 ወደ 25,000 እንደሚጠጋ ጠቁመዋል።
ወደ ተደራጀ የፋይናንስ እቅድ ከመግባታችን በፊት ከነሐሴ 1935 ጀምሮ ፕሬዝዳንት ሩዝቬልት የማህበረሰብ ጥቃቄ ድንጋጌን ባፀደቁበት ጊዜ መላው አሜሪካውያኑ የሚተማመኑባቸው ሁለት ነገሮች ላይ እናተኩር። በጊዜው አሜሪካውያን በዋነኝነት ልጆቻቸው ላይ እና የማህበረሰብ ጥቅማ ጥቅም ላይ ነበር እምነታቸውን የጣሉት። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ሁለቱም ለዚህ ትውልድ አስተማማኝ አይደሉም።
አስር ልጅ መውለድ የተለመደ በነበረበት ግዜ ከ አስሩ አንዱ በሽምግልና ወቅት ወላጆቹን ጧሪ ሆኖ መመልከት አስቸጋሪ አልነበረም። አሁን ግን አምስት ልጅ መውለድ በራሱ እንደ ተራራ ቢከብድም ከወለዱት መሀል እንክዋን በልጆቼ እጦራለሁ የሚል እምነት ያለው ጥቂት ወላጅ ነው። አሁን ላይ ልጆች ለኑሮ የሚያወጡት ወጪ ከዚህ ቀደሙ በመጨመሩ ለወላጆቻቸው ጧሪ እንዳይሆኑ አንዱ እንቅፋት ሆኖም መቷል። ልጆች ለመኖርያ ቤት፣ ለጤን መድህን፣ ለትምህርት ቤት እና ለሌሎች ወጪዎቻቸው ከቀን ቀን እየጨመሩ በመምጣታቸው እንክዋን ለወላጆች ለራሳቸውም እንዳይደርሱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
ይህ ሁኔታ ማህበራዊ ዋስትና ቢኖርም እንክዋን ለኑሮ በቂ እንዳልሆነ ግልፅ አድርጎታል። የመህበራዊ ዋስትና አላማው ለተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋዥ መሆን የነበረ ቢሆንም በርካቶች እንደ ብቸኛ የገቢ ምንጭ አድርገው ሲጠቀሙት ይስተዋላል። የገቢ እና የፕሮግራም ተሳትፎ ዳሰሳ (SIPP) እንደሚለው “የጡረታ ዋስትና ብሔራዊ ተቋም (NIRS) 40.2% ጡረተኞች ገቢያቸውን ከማህበራዊ ዋስትና ብቻ እንደሚያገኙ አስታውቋል። ያንን ገቢ አሟጠው ተጠቅመው እንኳን መጠነኛ በሆነ መኖርያ ቤት ውስጥ ለመኖር በቂ ላይሆን ይችላል።” ከዚህ ባሻገር ግን ዛሬ ጡረታ ያልወጡ ሰዎች ጡረታ በሚወጡበት ግዜ ማህበራዊ ዋስትናው ምን ያህል ክፍያ ሊሰጥ እንደሚችል ማወቅ ብልህ ለመሆን ያግዛል።
በተቀበሉት እያንዳንዱ ቼክ ላይ ሲከፍሉ የነበረው የማህበራዊ ዋስትና በስምዎ ባለው መለያ ውስጥ አይቀመጥም። የተሻለ ምላሽ እንደሚኖረው ተስፋ በማድረግ መንግሥት ገንዘቡን ለተለያዩ የመንግሥት ፕሮጀክቶች የማውጣት አዝማሚያ አለው። ምንም እንኳን አረጋውያን ባለፉት አመታት የማህበራዊ ዋስትና ማረጋገጫቸውን እየተቀበሉ ቢሆንም ይህ ለወደፊቱ ያን ያህል ተስፋ ሰጪ ላይሆን ይችላል።
ከሶሻል ሴኪዩሪቲ የተገኘ ዘገባ እንደሚያመለክተው “በ1946 እና 1964 መካከል የተወለዱ ጡረተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በሶሻል ሴኩሪቲ ሲስተም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሸክም እንደሚፈጥሩ ተገምቷል።” ፕሮግራሙ ከደምወዝ ታክሶች ከሚያስፈልገው በላይ እንዲያወጣ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የሶሻል ሴኩሪቲ እስከ 2034 ድረስ ሙሉ ክፍያ መፈጸም ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ከ2034 በኋላ ግን ክፍያውን ሙሉ ለሙሉ ስለመፈጸሙ እርግጠኛ መሆን አይቻልም።
ይህም በ 2034 እድምያቸው 62 ለሚሆኑ ሰዎች እድል ፊቷን እንድታዞር አስገድዷል። ካልሆነም ቃል ከተገባው ያነሰ መጠን ክፍያን እንዲያገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል። ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በ 2034 የመጠባበቂያ ገንዘቦች ይቀንሳሉ! ይህም አጠቃላይ ገቢው ከክፍያው ጋር ያልተመጣጠነ እንዲሆን ያደርገዋል። ለዚህ ብቸኛው መፍትሄ ጥቅማ ጥቅሞችን ከ 75 እስከ 80% መቀነስ ነው።
ብልህ ከሆኑ ይህ የጡረታ ክፍያ መጠን መቀነስ ስጋት ላይ ላይጥልዎ ይችላል። ተጨማሪ የፋይናንስ ደህንነትን የሚሰጥ የመጠባበቂያ እቅድ ሊኖረን ይገባል። ለመኪኖቻችን መካኒክ እና ጤናችንን ለማስጠበቅ ደግሞ ሀኪም እንዳለን ሁሉ ሀብታችንን ለማስጠበቅ ከፋይናንስ አማካሪ ጋር መማከር አዋቂነት ነው። ነገር ግን አማካሪ ለማግኘት ፍቃደኛ ካልሆኑ የጡረታ ግዜዎን በምቾት ለማሳለፍ አስተማማኝ እቅድ ማውጣት ይኖርቦታል። በጡረታዎ ጊዜህ አሁን እንደሚኖሩት በምቾት ለመኖር ማለም ብቻውን ካለ እቅድ ዋስትና ሊሆን አይችልም።
ማኅበራዊ ዋስትና ገቢዎን ለመደገፍ ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው አንዳንድ አማራጮች፦
401 ኬ
ኢንቨስት ለማድረግ በጣም ቀላሉ ከሆኑ ነገሮች አንዱ 401 (k) ነው። ኩባንያው የተሻለ በሆነ ቁጥር ጥቅሞቹም የተሻለ ይሆናሉ። አብዛኛዎቹ ኩባንያዎች እርስዎ ያፈሰሱትን መዋዕል እኩሌታ ይሰጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከእርሶ ከፍ ባለ መጠን ያተርፋሉ። ለምሳሌ Chick-Fil-A እስከ 5% ሲያተርፍ፣ Accenture እስከ 6%፣ እና AAA Club Alliance እስከ 7% በ401(kዎ) ላይ ባልዎት መዋዕል ልክ ያተርፋሉ። ገንዘቡ በቀላሉ ከቼኮ ውስጥ ስለሚወሰዱ እምብዛም አያስተውሏቸውም። እናም ከሰላሳ አመታት ጠንካራ ስራ በኋላ ከሶሻል ሴኩሪቲ በተሻለ ተመላሽ በሆነው 401(k)ዎ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊቀያስቀምጡ ይችላሉ።
አክሲዮኖች
በአክሲዮኖች አማካኝነት ገንዘብዎን ለረጅም ጊዜ ኢንቨስት ለማድረግ ደላላን መቅጠር አልያም በራስዎ ማድረግ ይችላሉ። አክሲዮኖች በተፈጥሯቸው ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። ነገር ግን በ ኤስ&ፒ 500 ውስጥ ያለው አማካይ ምላሽ ከ 1926 ጀምሮ 10-11% ነው። ስራውን በራሳቸው መስራት ላልፈለጉ ገንዘብዎን ወደ ኤስ&ፒ 500 ኢንቨስት ወደ ሚያደርግሎ ደላላ ጋር መሄድ ይችላሉ። ይህም አማካይ ተመለሻ ላይ የመድረስ ወይም ደግሞ የበለጠ እድል ሊሰጥዎ ይችላል።
በ ኤስ&ፒ 500 የሚደረጉት ጥብቅ ኢንቨስትመንቶች አዝጋሚ ሆነው ቋሚ ተመላሽ ሊሰጡዎት ቢችሉም ትልቅ ውጤት ለማግኘት የተወሰኑ ገንዘቦችን ለማጣት ፈቃደኛ ከሆኑ ሌሎች ኢንቨስትመንቶችን መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ T-Mobile ከአሥር ዓመታት በፊት፣ በ2011፣ የአክሲዮን ዋጋቸው በአንድ ድርሻ 23 ዶላር ነበር። በሐምሌ 2021 በ አንድ ድርሻ 144 ዶላር ነበር። ስለዚህ 200 አክሲዮኖችን በ$23 ገዝተው ቢሆን በአጠቃላይ 4,600 ማለትም ኢንቨስትመንት አንዳንዶች በአንድ አመት የግብር ተመላሽ ከሚያገኙት ያነሰ ማግኘት ይችላሉ። በ2021 ደግሞ የ28,000 ዶላር ተመላሽ ያገኛሉ። መጥፎ አይደለም! አሁን ሌላ አስር አመት መጠበቅ እና በ 2031 ማውጣትን አስቡት። ምናልባት ያ መጠን በእጥፍ ወደ $56000 ሊደርስ ይችላል። ምንም እንኳን በአጠቃላይ አክሲዮኖች አደገኛ ቢሆኑም እጅግ በጣም አነስተኛ ያለመሳካት አጋጣሚ ያላቸው በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የእድገት እድሎች ያሏቸው እንደ አፕል፣ ማይክሮሶፍት፣ አማዞን እና ሌሎች በርካታ ኢንቨስት የሚገባቸው በደንብ የተመሰረቱ ኩባንያዎች አሉ። በአክሲዮን ገበያ ውስጥ ያለው ገንዘብ ቀስ በቀስ እያደገ ሲሆን በባንክ ሒሳብ ውስጥ የተቀመጠው ገንዘብ በዋጋ ግሽበት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋ እያጣ ነው።
መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ይህ ለሁሉም ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ሪል እስቴት ከሌሎች በተለየ ሁኔታ በየግዜው እየጨመረ ይሄዳል። እ.ኤ.አ. በ 2008 የተከሰተው ትልቁ የምጣኔ ሀብት ውድቀት ሁሉም ላይ ጠባሳውን ቢያሳርፍም ዳግመኛ ግን አገግሟል። ዛሬ ላይ ቤቶች አይተን በማናውቀው ሁኔታ ዋጋቸው እየጨመረ ነው።
በጥሩ ሰፈር ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት ንብረት አስቡበት። በጡረታ ጊዜ ከሶሻል ሴኩሪቲ እና 401 በተጨማሪ ንብረቱን በማከራየት ገቢ ማግኘት ይችላሉ። ወይም ከ 30 ዓመታት በኋላ መሸጥ እና ትልቅ ትርፍ ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ በ Clarkston, GA በ90ዎቹ መጀመሪያ 80,000 ዶላር የነበሩ ቤቶች ዛሬ ወደ $300,000 ይጠጋሉ። ስለዚህ በጡረታ ጊዜ, ለማከራየትም ይሁን ለመሸጥ ቢወሰኑ አትራፊ መሆኖ አይቀሬ ነው።